የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ባሉት ዓመታት አየር መንገዱን በሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመሩ የቀድሞ አመራሮች የዕውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር አካሄደ።
በመርሓ ግብሩ ላይ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ፣ ካፒቴን ዘለቀ ደምሴ ፣ ዶ/ር አህመድ ኬሎ ፣ አቶ ብስራት ንጋቱ ፣ አቶ ግርማ ዋቄ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በመሩባቸው አመታት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት እና አለም ዓቀፍ ዝና ላበረከቱት የማይተካ የመሪነት አስተዋፅዖ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል ።
ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባ ስምንት አመት በላይ በበርካታ ደማቅ ስኬቶች ታጅቦ ዛሬ ለደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ በቅቷል። ይህ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የአየር መንገዳችን ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ አሁንም በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል! #የኢትዮጵያአየርመንገድ