Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ 200 የሚደርሱ ጋቦናውያን ተማሪዎችን በደማቅ ስነስርዐት ተቀበለ። ጋቦናውያኑ ተማሪዎች በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች በዩኒቨርስቲያችን ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በአቀባበል ስነስርዐቱ ላይ በኢትዮጵያ የጋቦን ሪፐብሊክ አምባሳደር ክብርት ሊሊ ስቴላ ንዶንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የአየር መንገዳችን ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
ሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪካ መዳረሻችን የሆነችው የጋና ዋና ከተማ አክራ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በከፍተኛ ድምቀት በኮቶካ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተቀብላለች።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደሆነው ታንዛኒያ ኪሊማንጃሮ የአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከፍ ብለን ለመብረር ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲሸልስ “አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: በዚህ ልዩ ቅናሽ የ 2 ምሽት ቆይታ በማድረግ ዘና ይበሉ! ስለ ልዩ የጉዞ ጥቅሉ ተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኙ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችንን አሊያም የጉዞ ወኪልዎን ማግኘት ይችላሉ።
ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በምቾት ይጓዙ ። ቀጣይ የጉዞ መዳረሻዎን የት አስበዋል?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ ኅዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ በቡድን ወደ ሲንጋፖር ከተማ ለሚጓዙ ደንበኞቹ ልዩ የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል። ትኬትዎን አሁኑኑ ይግዙ ፤ ጉዞዎን ከኅዳር 22 ቀን እስከ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ያድርጉ። በድረ ገፃችንን www.ethiopianholidays.com ፣በኢሜል አድራሻችን ETHolidays@ethiopianairlines.com እንዲሁም በስልክ ቁጥሮቻችን +251115174207/4203/4504 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ