የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲጂታል አማራጮቹ በተጨማሪ በአዳዲስ የሽያጭ ቢሮዎች ይበልጥ ወደ እርስዎ ቀርቧል። በሜክሲኮ ከንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ወደ አፍሪካ ህብረት በሚወስደው መንገድ ላይ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ ወደ አያት በሚወስደው መንገድ ፀሀይ ሪል ስቴት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል በከፈትናቸው አዳዲስ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦይንግ እና ቲንክ ያንግ በቅንጅት ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ለተውጣጡ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች (STEM) ልዩ ስልጠና በመስጠት ተማሪዎችን አስመርቀዋል። ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ስልጠናውም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩነቪርሲቲ በኩል ተሰጥቷል። ይህ STEM የተሰኘ ፕሮግራም አሁን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን የትምህርት ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ላሉ ወጣቶች ልዩ ትኩረት ያደርጋል። በዚህ በ2ኛው ዙር ከተመረቁ ተማሪዎች ውስጥ 50% ሴቶች ናቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዘንድሮው የ “World Travelers Award” ሽልማት ከታጨንባቸው ስድስት ዘርፎች አንዱ በአፍሪካ ምርጡ የኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ ዘርፍ ነው። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን አየር መንገድዎን ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሽልማት ውድድሮችና መድረኮች በአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ በመሪነት የተቀመጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው የ “World Travel Awards” ሽልማት ከዚህ ቀደም ለአራት ጊዜያት በ”ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ ሽልማትን የተቀዳጀ ሲሆን ዘንድሮም እጩ ሆኖ ቀርቧል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን አየር መንገድዎን ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገራችንን አቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት ከፍ ለማድረግ አዳዲስ ኤርፖርቶችን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመገንባት ለአገልግሎት እያበቃ ሲሆን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ጨምሮ ነባር ኤርፖርቶችና የመንገደኛ ማስተናገጃ ተርሚናሎችን በከፍተኛ ወጪ እያስፋፋና እያዘመነ ይገኛል።
የአዳዲስ አቪዬሽን መሰረተ ልማቶች መገንባትና የማስፋፊያና ዝመና ተግባራት መጠናቀቅ የበለጠ ምቹ እና ተደራሽ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ከማስቻሉም በላይ ንግድና ቱሪዝምን ለማሳደግ የጎላ ሚና ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት ኤርፖርቶችን ለማስፋፋትና ለማዘመን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተተገበሩ ያሉት ስትራቴጂክ መዋዕለ ንዋዮች የደንበኞች አገልግሎትን ምቹ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ የላቀ እገዛ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለክላውድ ናይን” (ቢዝነስ ክላስ) መንገደኞቹ ነፃ የበረራ ላይ ገመድ-አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እየገለፀ ደንበኞች በአገልግሎቱ በመጠቀም አስደሳች የበረራ ቆይታ እንዲያሳልፉ ሲጋብዝ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባንግላዴሽ ዋና ከተማ ወደሆነችው ዳካ ከተማ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ እንደሚጀምር ሲያበስር በደስታ ነው። ይህ አዲስ የበረራ መስመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ እስያ ያለውን ተደራሽነት የሚያሰፋ ሲሆን በባንግላዴሽ እና አፍሪካ መካከል ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://rb.gy/uoqkmg
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አለም አቀፍ ጥራቱን ጠብቆ የሚታተመውና ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ላይ ለንባብ እየቀረበ የሚገኘው ሰላምታ መፅሔት በዘንድሮው ሽልማት በአፍሪካ በበረራ ላይ በሚቀርቡ መፅሔቶች ውድ ድር ዘርፍ ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። ለዘመናት ተወዳጅ ሆኖ ለዘለቀው ሰላምታ መፅሔት ከታች በተቀመጠው ሊንክ ድምፅዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሰላምታ #ሰላምታመፅሔት
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሰላምታ #ሰላምታመፅሔት
በዘንድሮው የ “World Travelers Award” ለሽልማት ከታጨንባቸው ስድስት ዘርፎች አንዱ በአፍሪካ ምርጡ የኮንፈረንስ ሆቴል ሲሆን በዚህ ዘርፍም የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ዕጩ ሆኗል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትህትና በተላበሰ ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ሊያገለግልዎ ሁሌም ዝግጁ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን ለጠበቀ አስደሳች በረራ ጊዜ ምን ጊዜም ከእኛ ጋር ይጓዙ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ. ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ኤርትራ በየቀኑ የሚያደርገውን በረራ ለመቀጠል ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች አስመራ ውስጥ ስላጋጠሙት ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ማቋረጡን ለክቡራን ደንበኞቹ ከይቅርታ ጋር ይገልጻል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ለመጓዝ ቀድመው ትኬት ለቆረጡ ውድ መንገደኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌሎች አየር መንገዶች የሚጓጓዙበትን ሁኔታ ያመቻቻል። አለያም እንደአማራጭ በውድ ደንበኞቹ ፍላጎት ለትኬት የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉውን ተመላሽ ያደርጋል።
ድረገጻችንን በመጎብኘት www.ethiopianairlines.com አልያም ወደ ዓለም-አቀፍ የጥሪ መቀበያ ማዕከላችን በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በዚህ አጋጣሚ ከአየር መንገዳችን አቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ በውድ ደንበኞቻችን ላይ ለሚፈጠረው መጉላላት አየር መንገዱ ከልብ ይቅርታ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ወደ አስመራ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ክቡራን የአስመራ መንገደኞቻችንን ከሙጉላላት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ የበረራ አማራጭ እያቀረብን ሲሆን የመንገደኞቻችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በተለያዩ አየር መንገዶች ወደ መዳረሻቸው የማድረስ ስራችንን ቀጥለናል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ውድ የኤርትራ መንገደኞቻችን ወደ ዓለም-አቀፍ የጥሪ ማዕከላችን 6787 በመደወል እና 5 ቁጥርን በመጫን ለእናንተ ብቻ ተብሎ በተዘጋጀ ልዩ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ጉዟችሁን ለማቅለል ተዘጋጅተናል።
ሌሎች ውድ መንገደኞቻችን ይህንን ወቅታዊ ጉዳይ እስክንፈታ ድረስ በ6787 ብቻ በመደወል የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ እያስታወስን በዚሁ አጋጣሚ ለአስመራ መንገደኞቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ ለሚያጋጥማችሁ መጉላላት በድጋሚ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል