Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.76K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለ83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሕበራዊ ሀላፊነቱን በተለያዩ ግዜያት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን የሚወጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ 2015 ዓ. ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ ላይ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላትና ሰራተኞች ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወዳሰቡት መዳረሻዎ በምቹ አገልግሎት እና በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነ የሰርግ ዝግጅት የሶስት ሰራተኞቹን የጋብቻ ስነ ስርዓት በድምቀት ያከበረ ሲሆን በስካይላይት ሆቴል የተደረገውን ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ተከትሎ ጥንዶቹ አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሶስት ምሽት የጫጉላ ሽርሽር የጉዞ ጥቅል ወደ ዛንዚባር ተጉዘዋል። የሙሽሮች የዛንዚባር ቆይታ እንዳያመልጥዎ ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባዘጋጀው ልዩ ቅናሽ ተጠቅመው በመጪው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ በመታደም ልዩ ግዜ ያሳልፉ። ትኬትዎን እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ይግዙ ከ ሰኔ 24 ቀን እስከ ሐምሌ 12 ፣2016 ዓ.ም ይጓዙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ