Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያስፋፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ደግሞ በምስራቋ ኮኮብ ሱማሌ ክልል ከጂግጂጋ እና ጎዴ ቀጥሎ ወደ ቀብሪ ደሀር ከተማ ከሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ለሁለት ቀናት የበረራአገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ያበስራል። ትኬትዎን በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን፣ በድረ ገፃችን አሊያም በትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን ይግዙ።

https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
www.ethiopianairlines.com

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
55👍41👏6🎉4😍2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካሜሩን የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል ወደሆነችው ዱዋላ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 11 ከፍ እንደሚያደርግ ሲገልፅ በደስታ ነው። አየር መንገዳችን በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማዋ 7 ሳምንታዊ በረራዎች ያደርጋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👏4026👍22🥰3🎉3
በየትኛውም ግዜ በፈገግታ የታጀበ አገልግሎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
77👍18👏6🎉2🥰1
ዓለም አቀፉን የአብራሪዎች ቀን (world Pilots' Day) ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከመጡ ታዳጊ ተማሪዎች ጋር ቀኑን በጋራ አክብሯል። ታዳጊ ተማሪዎቹ የአየር መንገዳችንን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ከአብራሪዎችም ጋር የጥያቄና መልስ ውድድርን ጨምሮ ልዩ ቆይታ አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታዳጊ ተማሪዎች እና ወጣቶች የሀገራችን ብሎም የአፍሪካ ኩራት የሆነውን አየር መንገድ ተረክበው እድገቱን ያስቀጥሉ ዘንድ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ማድረጉን ይቀጥላል።
መልካም ዓለም አቀፍ የአብራሪዎች ቀን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
107👍38🥰13👏13🎉7😍6
በርካታ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ከአስደሳች የበረራ ቆይታዎች ጋር!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
🥰4528👍27🎉6👏4😍2
ከእኛ ጋር የሚኖርዎትን ቆይታ በልዩ መስተንግዷችን ምቹ እና አስደሳች ለማድረግ ሁሌም እንተጋለን።መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
93👍25🥰8🎉4👏3
ወደ ቀጣይ የጉዞ መዳረሻዎ ከእኛ ጋር ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍6232🥰6🎉1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አከበረ። በክብረ በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላት፣ የሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
59👍32👏4🎉3
ጊዜ አይሽሬ ውብ ትዝታዎቻችን!
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
88👍15🥰8👏3