Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዚሁ አጋጣሚ በረራ ያላችሁ ውድ ደንበኞቻችን ዛሬ ከሰዓት እና ነገ ጠዋት የመንገድ መጨናነቅ ሊኖር ስለሚችል የበረራ መስተጓጎል እንዳያጋጥማችሁ ከተለመደው ሰዓት ቀድማችሁ ወደ ኤርፖርት እንድታመሩ በትህትና እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደሚያስደስትዎ መዳረሻ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 18, 2016 ዓ .ም ጀምሮ ወደ ጋና አክራ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ያሳድጋል። በዚህም መሰረት በቀን ሁለት ጊዜ በመብረር ሳምንታዊ ምልልሱን ወደ 14 የሚያሳድግ ይሆናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከ 130 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች! ምርጫዎን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያድርጉ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የእንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል ክብርት ሶፊ ሄሌን ራይስ ጆንስ ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርና በአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልእክተኛ ዳረን ዌልች እና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ አመራር አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ማጠቃለያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራ ማድረግ የጀመረበት 50ኛ ዓመት በኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርስቲ ተከብሯል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጅስቲክስ አገልግሎት በአረቢያን የጭነት ሽልማት ውድድር በሶስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። ዘርፎቹም በፍጥነት እያደገ ያለ ዓለም አቀፍ የጭነት አየር መንገድ ፣ ምርጥ የህክምና ቁሳቁሶች ጭነት አየር መንገድ እና በአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ ናቸው። ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስቱ ዘርፎች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድምፅዎን ይስጡ።
https://rb.gy/m3tue
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ ዕይታ ያጋሩን ጋሬብ አሕመድ ናቸው እናመሰግናለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET-ABY ዳግላስ አውሮፕላን ሚያዝያ 16 ቀን 1965 ዓ.ም ለመጀመሪያ የበረራ ደህንነት ፍተሻ ወደ ጥገና ክፍል ሲገባ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲሺየልስ ከሚያደርገው እለታዊ በረራ በተጨማሪ ከጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አራት ሳምንታዊ የማለዳ በረራዎችን በመጀመር አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራውን ወደ 11 ከፍ እንደሚያደርግ ሲገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ