Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
አብራሪዎች የቅድመ በረራ ፍተሻ በማድረግ ላይ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እየገለጸ፣ ክቡራን መንገደኞቻችን እንደተለመደው ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቻችንን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟችሁ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ዕገዛ የምትሹ መንገደኞቻችን በአቅራቢያችሁ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከላችን (6787) በመደወል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!

ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም.

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደሚወዱት መዳረሻዎ ልናደርስዎ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እየገለጸ፣ ክቡራን መንገደኞቻችን እንደተለመደው ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቻችንን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟችሁ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ዕገዛ የምትሹ መንገደኞቻችን በአቅራቢያችሁ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከላችን (6787) በመደወል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!

የክቡራን መንገደኞቻችንን ፍላጎት በማጤን በድጋሚ ወደከፈትናቸው የአገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የበረራ ምልልሶቻችንን ለመጨመር ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡


ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም.
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ባልተቋረጠ ትጋት እና ስኬት የደመቀ ጉዞ ! መልካም የስራ ሳምንት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET-AAP ዳግላስ DC-3 አውሮፕላን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1968 ዓ.ም ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ በሚገኝ አየር ማረፊያ ሲያርፍ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ አፍሪካ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ. ቱሪዝምንና ንግድን በማቀላጠፍ የአገር ገጽታን የሚገነባ፣ ዘርፈ ብዙ እና ዓለም አቀፍ የንግድ ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል በአዲስ አበባ ለማቋቋም የሚያስችላቸውን የጋራ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረሙ።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://shorturl.at/AMNT5
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሁሌም በፈገግታ በታጀበው አገልግሎታችን ይደሰቱ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አየር መንገዱ በቂሊንጦ 2 የኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን አካላትን የሚያመርትበት መሬት በሊዝ ለመረከብ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን አካላትን በማምረት ለቦይንግ ድርጅት እያቀረበ እንደሆነ ይታወቃል፤ ሆኖም ምርቱ እያደገ ስለሚሄድና ከዚህ በፊት ሲያመርታቸው ከነበረው የአውሮፕላን አካላት ተጨማሪ ሌሎች ምርቶችንም የማምረት ዕቅድ ስላለው ይህን ሰፊ ዕቅድ የሚመጥን የማምረቻ ስፍራ በኢንዱስትሪ ፓርኩ መገንባቱ አየር መንገዱ ምርቶቹን በስፋት ለማምረት፣ በዚህም ከፍተኛ የሆነ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ከዘርፉም የሚያገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ ያስችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚሁ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር የ15ሚለዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚያደርግ ይሆናል፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ19ኛዉ የቡዳፔስት የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ10 ሺ ሜትር ሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ፣ ለተሰንበት ግደይ ብር እና እጅጋየሁ ታዬ ነሃስ በማምጣት ባስመዘገቡት አኩሪ ድል የተሰማውን ታላቅ ደስታ ይገልፃል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርስቲ ፣ የአቪየሽን ዘርፍ የልህቀት ማዕከል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቹ እና አስደሳች የበረራ ሳምንት በኢትዮጵያ አየር መንገድ!
በፈገግታ ታጅበዉ ከእኛ ጋር ይጓዙ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @MwakaMorris ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በሚያምር ኢትዮጵያዊ ፈገግታ በታጀበው መስተንግዶአችን ይደሰቱ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ምቹ እና አስደሳች የበረራ ጊዜ ያሳልፉ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ