Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ቦይንግ እና “ቲንክ ያንግ” ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ ታዳጊዎች እና ወጣቶች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንጅነሪንግ ዙሪያ የተዘጋጁ ስልጠናዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ ሊሰጡ ነው። ስልጠናው በአቪየሽን ፣ በቴክኖሎጂ እና ተያያዥ የስራ መስኮች ላይ ዝንባሌ ላላቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች እገዛ የሚያደርግ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አየር መንገዱ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳትፎውን ቀጥሏል።እንደባለፈው አመት በዘንድሮ የክረምት ወቅትም 100 ሺህ ችግኞችን በተለያዩ ሥፍራዎች ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል።በዚህም የአየር መንገዱ አመራሮች ፣ሠራተኞች እና የቦርዱ አባላት በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በመገኘት ከከተማው ፣ከክፍለ ከተማው እና ከወረዳው አመራር ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን ተናግረዋል። የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ