Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.82K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ "2022 ዓለም አቀፍ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ውድድር" የአመቱ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ ዘርፍ እና የአየር እቃ ጭነት ኢንደስትሪ የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ለሁለት ሽልማቶች ታጭቷል። ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ድምፅዎን ይስጡ!
https://www.aircargoweek.com/awards-2022/2022-awards-voting/
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ።#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
ከመሬት በብዙ ሺህ ጫማ ከፍ ብለው ጣፋጭ ምግቦቻችንን ከግሩም መስተንገዶ ጋር ያጣጥሙ፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተቋርጦ የነበረውን በረራ ከ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደቀጠለ ስናበስርዎ ደስታይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር አለምን ይጎብኙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
ልዩ እና ኢትዮጵያዊ በሆነው መስተንግዷችን ታጅበው ይጓዙ፡፡ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምቾት ይብረሩ! ቀጣዩ ጉዞዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @ i_am_dynapix ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከጤና ጋር በተያያዘ ምክንያት ላለፉት ስድስት ወራት በሀገረ አሜሪካ በህክምና ላይ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጤናቸው ላይ ሙሉ ትኩረት ማድረግ ስለፈለጉ ያልተከፋፈለ ትኩረት የሚጠይቀውን የአየር መንገዱን የአመራር ሂደት ማስቀጠል አልቻሉም፡፡ በዚህም ምክንያት ያቀረቡት የቅድመ ጡረታ ጥያቄ (Early retirement) ዛሬ መጋቢት 14፣ 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ማኔጅመንት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ባስተዳደሩበት 11 አመታት አየር መንገዱ ከአንድ ቢልየን ዶላር አመታዊ ገቢ ወደ 4.5 ቢልየን ዶላር አመታዊ ገቢ ፣ ከ33 አውሮፕላኖች ወደ 130 አውሮፕላኖች፣ ከ3 ሚልየን መንገደኛ ወደ 12 ሚልየን መንገደኛ (ከኮቪድ19 ወረርሺኝ በፊት) እንዲሁም በሌሎች የመለክያ ዘርፎች የአራት እጥፍ አስደናቂ እድገት ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ በተጨማሪም አየር መንገዱ የአፍሪካ ትልቁን ሆቴል፣ የእቃ ጭነት ተርሚናል፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል፣ የአቪዬሽን ትምህርት ማዕከልን እና ሙሉ ምስለ በረራን ጨምሮ ከ700 ሚልየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው መሰረተ-ልማት ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ማኔጅመንት አቶ ተወልደ ገብረማርያምን የሚተኩትን አዲሱን ዋና ስራ አስፈፃሚ በቅርቡ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
የቀድሞ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ማኔጅመንት ሊቀመንበር ሆነው በኢትዮጵያ የመንግስት የልማት ተቋማት አስተዳደር ኤጀንሲ በቅርቡ ተሾመዋል፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የካበተ ልምድ ባለቤት የሆኑ፣ ስኬታማ እና መልካም ዝና ያተረፉ አንጋፋ ግለሰብ ሲሆኑ አየር መንገዱን ለ7 አመታት በዋና ስራ አስፈጻሚነት በመምራት ለፈጣንና ትርፋማ እድገቱ መሰረት መጣላቸው የሚታወስ ነው፡፡ የአቶ ግርማ ዋቄ የስራ ልምድ ፣ ትጋት እና በተግባር የተፈተነ የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎት ቦርዱን በብቃት በመምራት አየር መንገዱን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ማኔጅመንት ፣ አመራርና እና ሰራተኞች ለአቶ ተወልደ ልባዊ ምስጋናቸውንና መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ በፍጥነት ወደ ቀድሞ ጤንነታቸው እንዲመለሱ ይመኛሉ፡፡
👍52
በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሔደው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአለም በአንደኝነት ያጠናቀቀውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በማስተናገዳችን ትልቅ ክብር ተሰምቶናል! ኮርተንባችሗል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍3
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/mesfin-tasew-appointed-as-new-ceo-of-ethiopian-airlines-group

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
3👍1
ለቀጣይ መዳረሻዎ ዝግጁ ይሁኑ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስታር አላያንስ B787-8 አውሮፕላን በሮም አውሮፕላን ማረፊያ፡፡
ምስል በ@hessenflyer
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከብራዚል መንግስት “ሪዮ ብራንኮ” የተሰኘው የሀገሪቱ ከፍተኛ የክብር ሜዳይ ሽልማት ተበረከተለት። ሽልማቱ የተበረከተው ለቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለነበሩት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና በብራዚልና በደቡብ አሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኦፕሬሽናል ዳይሬክተር ለነበሩት አቶ ግሩም አበበ ነው።
ሽልማቱ የተበረከተው ብራዚል በኮቪድ-19 በተፈተነችባቸው ወቅቶች ብራዚላውያንን ወደ ሀገራቸው በማጓጓዝና የኮቪድ-19 ክባትንና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ብራዚል በማድረስ አየር መንገዱ ለተጫወተው ጉልህ ሚና ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ወደየሀገሮቻቸው በማጓጓዝና የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶችን በመላው ዓለም በማድረስ ወረርሽኙን ለመከላከል በተደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደነበረው የሚታወስ ነው።
👍21
የስኬት ሳምንት ይሁንልዎ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 Thewodros S. Girma
በፈገግታ ታጅበው ከእኛ ጋር ይጓዙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ