Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.8K subscribers
3.86K photos
145 videos
2 files
416 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 Freighter የተሰኘውን አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ምርት ለመግዛት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን እያስመዘገበ የሚገኘውንም ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ስምምነቱን አስመልክተው “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ካምፓኒ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ያሉ ሲሆን “ይህ አዲሱ ቦይንግ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ብለዋል።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-boeing-sign-memorandum-of-understanding-for-new-777-8-freighter
ከማራኪው ቢሮአችን ሰላምታችን ይድረሳችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ብሩህ እና ስኬታማ ሳምንት ተመኘንላችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #March8
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባህርና አየር የተቀናጀ ትራንስፖርት አገልግሎት (sea-air multimodal transportation) ለመስጠት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከጅቡቲ አለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት (IDIPO) እና ከጅቡቲ ኤር ጋር ተፈራረመ። ስምምነቱ ከቻይና በባህር ወደ ጅቡቲ የሚመጡ ጭነቶችን የአየር መንገዱን ሰፊና ዘመናዊ የካርጎ ጭነት አገልግሎት አቅም በመጠቀም ከጅቡቲ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በአየር ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው።
ከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዳሬሰላም፣ታንዛንኒያ የምናደርገውን እለታዊ በረራ ወደ ሁለት ከፍ የምናደርግ መሆኑን ስንገልፅ ደስታ ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @ Tabor ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
1
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን እ.ኤ.አ በ 1957 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በጎበኙበት ወቅት።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል የዘርፉን ብቁ ባለሙያዎች የያዘ እና በአቪዬሽን የጥገና መስክ በተሰማሩ አለም አቀፍ ተቆጣጣሪ አካላት ስለ አስተማማኝነቱ የተመሰከረለት ምርጥ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 #HilenaTafesse
👍3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት በአፍሪካ ትልቁ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ሰጪ ሲሆን የአቪየሽን ኢንደስትሪው የደረሰባቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ በማዋል ለደንበኞቹ ቀልጣፋና አስተማማኝ ግልጋሎት በመስጠት ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፈ ነው።
ምቾትዎን ጠብቀን እርስዎን በብቃት ማገልገላችን የሁልግዜም ኩራታችን ነው!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ብሩህ እና ስኬታማ ሳምንት ተመኘንላችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው ጉብኝት በማድረግ ከአየር መንገዳችን ማኔጅመንት አባላት ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ