Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.7K subscribers
3.83K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ውድ ደንበኞቻችን፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ ዓመት የምስረታ በአልን በማስመልከት ስጦታ እየሰጠ ነው በሚል የወጡ ሃሰተኛ መልዕክቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለማወቅ ችሏል። ስለሆነም በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች በማጭበርበር እንዳይታለሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኦፊሻል የኦንላይን መድረኮች ከዚህ በታች ያሉት መሆናቸውን እናሳውቃለን።

ድህረ ገፅ: https://www.ethiopianairlines.com/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ethiopianairlines
ትዊተር: https://twitter.com/flyethiopian
ቴሌግራም: https://t.me/ethiopian_airlines

Dear Customers,

Ethiopian Airlines has learned that fake messages from unknown sources are circulating through social media claiming that Ethiopian is giving gifts regarding 75th-anniversary celebration. This is, therefore, to inform our customers around the world not to be deceived by the scams. Please be informed that the below are the links to Ethiopian Airline’s official online platforms

Website: https://www.ethiopianairlines.com/
Facebook: https://www.facebook.com/ethiopianairlines
Twitter: https://twitter.com/flyethiopian
Telegram : https://t.me/ethiopian_airlines
👍3
ዘና ይበሉ፣በበረራዎ ይደሰቱ፦ ስለመረጡን እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ቀጣዩ ጉዞዎን ወደ የት ለማድረግ አስበዋል፧ የበረራ ሰራተኞቻችን ጉዞዎን ምቹ ለማድረግ ተዘጋጅተው እየጠበቁዎት ነው። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሳምንትዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይጀምሩ። ጥራት ያለው አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የ2021 የጋና ቁንጅና ውድድር first runner up አሸናፊ ዶክተር ሴቶር ኖርግቤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ ክፍሎችን በመጎብኘቷ ደስታ ይሰማናል።በውድድሩ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ቪድዮ ይህን ይመስላል።
https://youtu.be/gL_WS6M5W18
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350 የተሰኘውን ግዙፍና ዘመናዊ አውሮፕላን ከሚያበሩ አምስት ግዙፍ የአለማችን አየር መንገዶች አንዱ ነው። ይሕ ኤርባስ A350 አውሮፕላንም በዚህ መልኩ የቀለም ቅብ ተደርጎለት አለም አቀፍ በረራዎቻችንን ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ቪዲዮውን እንዲመለከቱ ጋብዘንዎታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://youtu.be/kxQdhBzpJd4
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን@WondimagegnFanta ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በከፍተኛ የአየር ጭነት ፍላጎት መጨመር ምክንያት መልካም በሚባል የፋይናንስ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝና በትርፋማነት እንደቀጠለ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጥር 3 ቀን 2014 ዓ. ም በዱባይ ኤክስፖ በተካሔደው የበይነ መረብ ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል። አየር መንገዱ ወረርሽኙን በራሱ የፋይናንስ ጥንካሬ የተቆጣጠረው ሲሆን፣ ከወረርሽኙ በፊት ካለው አቅሙ ወደ 70 በመቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
https://reut.rs/31PVk9U
1
ፈር ቀዳጅ ከሆኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች መካከል ወደ ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የመጀመሪያዎቹን በረራ ያደረገው የዲሲ- 6ቢ አውሮፕላን። #ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
ከምቹ የበረራ መስተንግዶ ጋር እንጠብቅዎታለን። የበረራ ምዝገባዎትን ከቤትዎ ሆነው በቀላሉ ይያዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.ethiopianairlines.com/aa
👍2
ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለጥምቀት በዓል አከባበር ለሚጓዙ ደንበኞቻችን ክብረ ወሰን ሆኖ የተመዘገበ በቀን 22 በረራዎች በማድረጋችን ደስታ ይሰማናል!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መልካም የከተራ እና ጥምቀት በዓል ይመኛል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍2
እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የላሊበላ ቅርንጫፍ ቢሮ ፣በ1960።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መድረሻዎን ይወስኑ፣ አብረውን ይጓዙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በስኬት ከፍታ ልቆ የሚታይ !#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍2
የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/,የአውሮፓ ህብረት አቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/, CAAC, ECAA እንዲሁም ሌሎች በርካታ የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ጥልቅ ምርመራና ፍተሻ ካደረጉና ዳግም ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ የማክስ አውሮፕላናችንን ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውናል፡፡ ለደህንነት ቅድሚያ እንደመስጠታችንና ማክስ አውሮፕላንን ወደ ስራ ለመመለስ ከመጨረሻዎቹ አየር መንገዶች ተርታ እንደምንሆን በገባነው ቃል መሰረት እስካሁን 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደበረራ በመመለስ ከ330 ሺህ በላይ በረራዎችን አድርገዋል፡፡ የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ መሃንዲሶች፣ የአውሮፕላን ጥገና ባለሞያዎች እንዲሁም የበረራ አስተናጋጆች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻችንን ወደ በረራ ለመመለስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተዋል፡፡ ከእኛ ጋር አብረውን እንዲበሩ ተጋብዘዋል፤ ለበረራው ሲመጡ እርስዎን ሞቅ ባለ አቀባበል ለመቀበል ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1