April 5
April 6
April 7
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የበረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን ሲያበስር ደስታ ይሰማዋል። ይህ አዲስ የበረራ አገልግሎት በሳምንት አራት ቀናት የሚደረግ ሲሆን መንገደኞች በተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ የደማቅ ባህል እና ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እድሎች ባለቤት ወደሆነችው ሻርጃ ከተማ በቀላሉ እንዲጓዙ ያስችላል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-prepares-to-launch-passenger-flight-service-to-sharjah-the-uae
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍46👏8❤7
April 8
April 8
April 10
ማሳሰቢያ
አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ለአንድ ሰዓት የሚቆይ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ የሙሉ አቅም ልምምድ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ልምምድ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ እና የእርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ብቁነትን፣ በአደጋ ጊዜ የሚኖር የመልዕክት ልውውጥ ፍሰትን እንዲሁም በእርዳታ ሰጪዎች መካከል የሚኖረውን ቅንጅት እና ጥምረት ለመፈተሸ ይረዳል፡፡
በተጨማሪም ልምምዱ ከአየር ማረፍያው ውጪ የሚገኙ እርዳታ ሰጪዎች ከአየር ማረፍያው አቀማመጥ እና በውስጡ ከሚገኙ የእርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ በእውነተኛ ድንገተኛ አደጋ ወቅት የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ የተፋጠነ እንዲሆን በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ይህንንም ለመፈተሽ በወቅቱ በከተማው ሆስፒታሎች እና በአየር ማረፍያው መካከል የእርዳታ መስጫ ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሚኖር መሆኑን እያሳወቅን ይህ እንቅስቃሴ የልምምዱ አካል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዲረዱልን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።
አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ መሰል ልምምዶችን በእየሁለት አመት አንዴ ያከናውናል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል!

👍107❤16👏10
April 10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዛሬው የኢትዮጵያ የተሰኝው ፕሮግራማችን በተለያዩ የአቪዬሽን ሙያ ላይ የተሰማሩ ሴት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ጋር ቆይታ አድርጓል ተከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
👍38❤5
April 10
April 11
April 12
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሃግብሮች “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ሽልማት መቀዳጀቱን ስናበስር በደስታ ነው። እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ ናቸው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-wins-prestigious-titles-at-two-award-events-in-hamburg-germany
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍79❤31👏17😍1
April 14
April 17
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታዊው የኢትዮጵያ ፕሮግራማችን በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ነው። ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
👍35❤4
April 17
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል። መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
❤72👍34👏2
April 19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት መርሀግብር አካሄደ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ኢቲ ፋውንዴሽን” በተሰኘው የስራ ክፍሉ አማካኝነት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በዚህ ማዕከል በቋሚነት በየዕለቱ የሚያደርገው የምገባ መርሀግብር ይገኝበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ኢቲ ፋውንዴሽን” በተሰኘው የስራ ክፍሉ አማካኝነት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በዚህ ማዕከል በቋሚነት በየዕለቱ የሚያደርገው የምገባ መርሀግብር ይገኝበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍87❤13🥰7👏7
April 20