Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በምቾት እና በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ታጅበው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ብሩህ የስራ ሳምንት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025 የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን ሲያበስር በደስታ ነው። ይህ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽኑ ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዕውቅና ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ http://tiny.cc/o8yvzz
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክፍል መንገደኞች የተዘጋጀ አዲስ የበረራ ላይ ዝርዝር የምግብ አማራጮችን የማስተዋወቅና የቅምሻ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል አካሄደ። መርሐግብሩ አዲሱን የበረራ ላይ ምግብ አማራጮች ከማስተዋወቅ ባለፈ ከኢኮኖሚ እና ቢዝነስ ክፍል መንገደኞቻችን ተገቢውን ግብረ መልስ ለማግኘት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ በርካታ መዳረሻዎቻችን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች ያስተዋወቀ ልዩ መርሐግብር በኪንሻሳ አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ በማስተዋወቅና አህጉሪቱን ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅዎ የተገለፀ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶችና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሰፊው ተዋውቀውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ