Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.58K photos
134 videos
2 files
399 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ 200 የሚደርሱ ጋቦናውያን ተማሪዎችን በደማቅ ስነስርዐት ተቀበለ። ጋቦናውያኑ ተማሪዎች በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች በዩኒቨርስቲያችን ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በአቀባበል ስነስርዐቱ ላይ በኢትዮጵያ የጋቦን ሪፐብሊክ አምባሳደር ክብርት ሊሊ ስቴላ ንዶንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የአየር መንገዳችን ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
ሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪካ መዳረሻችን የሆነችው የጋና ዋና ከተማ አክራ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በከፍተኛ ድምቀት በኮቶካ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተቀብላለች።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደሆነው ታንዛኒያ ኪሊማንጃሮ የአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከፍ ብለን ለመብረር ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ