Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትህትና በተላበሰ ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ሊያገለግልዎ ሁሌም ዝግጁ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማት መቀዳጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሲሸልስ “አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: የዚህ ልዩ ቅናሽ ሽያጭ ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 6፣ 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ጉዞዎን ከህዳር 1፣ 2017 እስከ ታህሳስ 22፣ 2017 ያድርጉ። ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
መግለጫ
በዛሬው ዕለት አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠው እና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን እያረጋገጥን በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገለፀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
በአፍሪካ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 ላይ ምቹ እና አይረሴ የበረራ ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን ጊዜያት ለመፍጠር ዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350-1000
ለአፍሪካ አሕጉር የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ልንረከብ እነሆ ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተውናል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኤርባስA350-1000 #በአፍሪካቀዳሚ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር የሚያቀርበውን ሳምንታዊ “የኢትዮጵያ” የተሰኘ በአየር መንገዳችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ፕሮግራም እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንግላዴሽ ዳካ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ዛሬ ምሽት ጀመረ። የበረራውን መጀመር በማስመልከት በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ሲክደር ቦዲሩዛማን፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ክፍል ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ደማቅ የበረራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተከናውኗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ልዩ፣ ምቹ እና አዝናኝ የበረራ ቆይታ ለአፍሪካ አህጉር የመጀመሪያ በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን! ሁለት ቀናት ብቻ ቀሩት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኤርባስA350-1000 #በአፍሪካቀዳሚ