Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንግላዴሽ ዳካ የጀመረው አዲስ በረራ ዳካ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ ታሪክ የቀዳሚነታችን ማሳያ ከሆኑት ስኬቶቻችን አንዱ የሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን እነሆ በነገው እለት አዲስ አበባ ይገባል!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኤርባስA350-1000 #በአፍሪካቀዳሚ
አስደሳች በረራ ከልዩ መስተንግዶ ጋር በኢትዮጵያ አየር መንገድ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በፈረንሳይ ቱሉዝ በተካሄደ ስነስርዓት ከኤርባስ ኩባንያ ተረከበ።

በርክክብ ስነስርዐቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዳችን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የኤርባስ ኩባንያ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተረከበው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል። አውሮፕላኑ አቪዬሽን ሳንስ ፍሮንቲርስ ከኤርባስ ኩባንያ ጋር በመተባበር ለኢቲ ፋውንዴሽን ያበረከቱትን ከ100,000 ዩሮ በላይ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁሶች ያጓጓዘ ሲሆን አዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ታላላቅ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ ሚኒስተሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርአት ተደርጎለታል። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/wr796e
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኤርባስA3501000
ማራኪ የጎርጎራ ኢኮ ሎጅ ዕይታ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #መስኮትምልከታ
📸Yonathan Menkir Kassa