የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሶስት ቀናት ወደ ሞንሮቪያ ላይቤሪያ የሚያደርገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር ሲያበስር በደስታ ነው።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-resumes-its-flight-to-monrovia-liberia_001
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሞንሮቪያ #ላይቤሪያ
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-resumes-its-flight-to-monrovia-liberia_001
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሞንሮቪያ #ላይቤሪያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 እጅግ ዘመናዊ የመንገደኞች አውሮፕላን ቅንጡ እና ምቾት ባላቸው የቢዝነስ እና የኢኮኖሚ ክፍል መቀመጫዎች፣ በማራኪ 4K ስክሪኖች እና ከፍተኛ ፍጥነት ባለው ዋይ ፋይ አገልግሎት እንዲሁም ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ታግዞ ምቾትዎ እንደተጠበቀ እርስዎን ለማገልገል ተዘጋጅቷል ፡፡#የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350
በአፍሪካ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ መሪነት የሚታወቀው የኢትዮጽያ አየር መንገድ ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተላበሰው አዲሱ A350-1000 አውሮፕላኑ እርስዎን ሊያገለግልዎ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ነው። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350
በኤር ባስ A350-1000 አውሮፐላን ኢኮኖሚ ክፍል በምቾት አይረሴ የበረራ ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን ጊዜያት ለመፍጠር ዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በምስጉን መስተንግዶአችን፣ እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላኖቻችን እና ከ140 በላይ በሆኑ መዳረሻዎቻችን እያንዳንዱ ጉዞዎን አይረሴ ለማድረግ ሁሌም እንተጋለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከሌጎስ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ሌጎስ በሳምንት ሰባት ቀናት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይብረሩ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ ለኢትዮጵያ) ስርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ ይሰራል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፋይዳ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፋይዳ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትህትና በተላበሰ ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ሊያገለግልዎ ሁሌም ዝግጁ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማት መቀዳጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።
ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሲሸልስ “አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: የዚህ ልዩ ቅናሽ ሽያጭ ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 6፣ 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ጉዞዎን ከህዳር 1፣ 2017 እስከ ታህሳስ 22፣ 2017 ያድርጉ። ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
መግለጫ
በዛሬው ዕለት አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠው እና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን እያረጋገጥን በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገለፀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል