Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት ልክ በዛሬው ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ከቦይንግ ተረከበ። ይህ ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቪዬሽኑ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ልህቀት ለአህጉራችን አፍሪካ በማስተዋወቅ ረገድ ያለውን ቁርጠኝነት እና ቀዳሚነት ያረጋገጠበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። አሁንም ለመንገደኞች ደህንነት እና ምቾት መረጋገጥ ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ አውሮፕላኖች ስራ ላይ በማዋል በአፍሪካ ብሎም በዓለም ደረጃ ያለንን የመሪነት ሚና አጠናክረን እንቀጥላለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ድሪምላይነር
ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ የአቪዬሽን ልህቀት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን ደህና መጡ። እኛን ምርጫዎ በማድረግ ዓለምን ይጎብኙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሼባ ማይልስ ሲልቨር ደንበቾቹ የተለያዩ የመዝናኛ እና ማረፊያ አገልግሎት የሚሰጥ የሲልቨር ላውንጅ አስመርቆ ለአገልግሎት አበቃ። ይህ ላውንጅ የተከፈተው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ ሲልቨር ደንበኞች መንፈስን የሚያድሱና እና ዘና የሚያደርጉ አገልግሎቶች የሚያገኙበት ስፍራ ነው። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/jqrjem
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሼባማይልስ
የእረፍት ቀናትዎን ወደ ውብ መዳረሻዎቻችን አብረውን በመብረር አዝናኝ ቆይታ ያሳልፉ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ
እ.ኤ.አ. ኦገስት 16 ቀን 2024 ዓ.ም. ጠዋት ከህንድ ሙምባይ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በዝግጅት ላይ ወደነበረ አውሮፕላን የሚጫኑ ሻንጣዎችን ይዞ ወደ አውሮፕላኑ በመጎተት ላይ በነበረ ጋሪ ላይ ከተጫኑ ሻንጣዎች በአንዱ እሳት ታይቷል። ክስተቱ ጋሪው ከራምፕ አካባቢ ወደ አውሮፕላኑ በመሄድ ላይ ሳለ እንደተከሰተ ተስተውሏል። ይህንንም ክስተት የተመለከቱ በሙምባይ ያሉ የደህንነት ፣ የጸጥታ እና የእሳት አደጋ ባለሞያዎች እሳት የያዘውን ሻንጣ በመለየት እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል። አውሮፕላኑ አስፈላጊው ተጨማሪ የደህንነት ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ እና አስጊ ነገር አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በረራውን አካሂዷል።
የሙምባይ ኤርፖርት ባለስልጣናትና የሚመለከታቸው አካላት የክስተቱን ምንጭ በመመርመር ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል
ደማቅ ፈገግታ በተላበሰው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን አይረሴ የበረራ ትዝታን ይሰንቁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከኢትዮጵያዊ ትህትና ጋር የካበተ ልምድ ባላቸው የበረራ መስተንግዶ ባልደረቦቻችን እንኳን ደህና መጡ እንላለን! ኑ ከእኛ ጋር ይብረሩ በረራዎን ምቹ እና አይረሴ እናደርጋለን። መልካም ሳምንት!
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በህንድ አራተኛ መዳረሻ ወደሆነችው ቸናይ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ በሳምንት አራት ቀን በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን ሲገልፅ በደስታ ነው።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Monametsi Sokwe ናቸው፤ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ውድ ደንበኞቻችን

ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 09፡00 ሰአት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ ተገደዋል።

ይህ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎቻችን ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። እንደተለመደው የመንገደኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎቻችን የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን።

በዚህ አጋጣሚ መንገደኞቻችን ላጋጠማቸው መጉላላት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
መሃላ በተግባር!
አቶ ለማ በቀለ አለሙ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴኪዩሪቲ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ የሥራ ባልደረባችን ሲሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምገባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት አስመስክረዋል። አቶ ለማ በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ መንገደኛ ረስተዉ የሄዱትን የእጅ ቦርሳ ውስጡ ከነበረው 71 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ምንም ሳያጎድሉ በሙሉ ለሚመለከተው የአየር መንገድ ቢሮ ያስረከቡ ሲሆን፤ አየር መንገዱም አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ንብረቱ ለውድ ደንበኛችን እንዲመለስ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎትን የዕድገቱ መርሕ አድርጎ በስኬት ጎዳና ላይ የሚገኝ ብሔራዊ ኩራት ነው። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጀመንት አባላት እና ሠራተኞች ለዚህ መልካምና አርዓያነት ላለው ተግባር የከበረ ምስጋና ያቀርባሉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ክቡራን መንገደኞቹ አዝናኝ የበረራ ቆይታ ይኖራቸው ዘንድ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሙዚቃ ስራዎች 140 ወደሚጠጉ ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቹ ለሚጓዙ መንገደኞቹ ተደራሽ የሚሆኑበትን አማራጭ ይዞ ብቅ ብሏል። በመሆኑም የሙዚቃ ስራዎቻችሁ አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ የምትፈልጉ የጥበብ ባለሙያዎች በሙሉ ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሙዚቃዎቻችሁን ይዛችሁ በመቅረብ የዕድሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።
ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥሮቻችን 0115178079/4079/8197 ይደውሉ። አሊያም በኢሜል አድራሻዎቻችን HiwotGe@ethiopianairlines.com ወይም
HilinaBel@ethiopianairlines.com ይፃፉልን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው “World Travel Awards” ሽልማት በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። ዘርፎቹም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ቢዝነስ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ብራንድ፣ ምርጥ የአፍሪካ የበረራ ላይ መዝናኛ መፅሔት ሰላምታ እና ምርጥ የአፍሪካ ኮንፈረንስ ሆቴል (የኢትዮጵያ ስካይ ላይት) ዘርፎች ናቸው። እርስዎም ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመጠቀም ድምፅዎን የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው አየር መንገድዎ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ