Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.4K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ እና በውብ ተፈጥሮ ታጅበው በምቾት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ድረ ገፅ https://www.ethiopianairlines.com/aa/book/booking/web-check-in አሊያም የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ተጠቅመው ቼክ ኢን በማድረግ ኤርፖርት ሲደርሱ ለዚህ አገልግሎት በተለዩ መስኮቶች ሻንጣዎን ቀድመው በማስረከብ ጉዞዎን ያቀላጥፉ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አቪዬሽን ታሪክ የስኬት እና ቀዳሚነት ምልክት ሆነን ዛሬ ላይ ደርሰናል። ለበለጠ ስኬት እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎትም እየተጋን እንገኛለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት። ይህ ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተሰጠ የላቀ አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላበረከተው ዘርፈ ብዙ አስተዋፅዖ ይህ ሽልማት ተበርክቶለታል። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። https://rb.gy/8gw7qk
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በተለመደው ምርጥ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ እና አስደሳች ለማድረግ ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቤልጂዬም ብራሰልስ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የቀጥታ በረራ በማሳደግ ወደ ከተማዋ ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ ዕለታዊ የቀጥታ በረራ እንደሚጀምር ሲገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በወንዶች ማራቶን በጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በእያንዳንዱ ግብይትዎ ማይል ያግኙ!
ዉብና ብራንድ የቆዳ ዉጤቶችን ከ ኬር ኤዥ ኢትዮጵያ ሲገዙ በእያንዳንዱ የ100 ዶላር ግብይት እስከ 30% የሚደርስ ቅናሽና ተጨማሪ 300 ማይሎችን ያግኙ! ግብይቶችን ሲፈፅሙ የሼባማይልስ አባልነት ቁጥርዎን ማስመዝገብዎን ያረጋግጡ:: ይህ ልዩ አጋጣሚ ከነሐሴ 2፣ 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ም ይቆያል፡፡
https://www.kerezhius.com/
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሼባማይልስ
በርካታ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ከአስደሳች የበረራ ቆይታዎች ጋር!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ደማቅ ፈገግታ በተላበሰው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን አይረሴ የበረራ ትዝታን ይሰንቁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚያስገነባው ሜጋ ኤርፖርት ከዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር የቴክኒካል፣ የአርክቴክቸር፣ የኢንጅነሪንግ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ስምምነት ተፈራረመ። ይህ ግዙፍ ኤርፖርት በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኛ ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን ይህም ኤርፖርቱ አሁን በዓመት የሚስተናገደውን መንገደኛ ቁጥር በአራት እጥፍ ያሳድገዋል።
ይህ አዲስ ኤርፖርት የሚገነባበት ስፍራ ከመሬት ወለል ያለው ከፍታ (lower altitude) ዝቅተኛ በመሆኑ ለአውሮፕላኖች እንቅስቃሴ ምቹ የሆነና የኤርፖርቱ አጠቃላይ ግንባታም አካባቢያዊ ተስማሚነትን ጠብቆ የሚከናወን ይሆናል።
ለበለጠ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ: rb.gy/6mytah
በፈረንሳይ ፓሪስ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገራችንን ወክሎ የተሳተፈው የኦሎምፒክ ቡድን ትናንት ምሽት ከፓሪስ ቻርልስ ደጎል አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲነሳ ደማቅ አሸኛኘት አድርጓል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐንሀገን፣ ዋርሳው እና አቴንስ የ” አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” ልዩ የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል። ይፍጠኑ የዚህ ልዩ ጥቅል ተጠቃሚ ይሁኑ! ትኬትዎን እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ይግዙ፤ በረራዎን ከመስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ያድርጉ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ፣ ኢስታንቡል እና ጆሀንስበርግ ለሚጓዙ መንገደኞቹ የ500 ማይልስ ሽልማት እንካችሁ ይላል። አሁኑኑ ምዝገባዎን በመያዝ ጉዞዎን ከሽልማት ጋር ያድርጉ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Akesse Moïse Sanza ናቸው፤ እናመሰግናለን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ