የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከተሞች ወደሆኑት ኒያሚ ፣ ባማኮ እና ዳካር በረራ በመጀመር አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት የበረራ አድማሱን ማስፋፋት በቀጠለበት ወቅት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
👍52❤17👏2🎉1
መግለጫ
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብራቸውን በታማኝነት ለሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ክብራቸውን የሚመጥን ልዩ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገለጸ” የሚል ዘገባ እንደተሰራጨ አስተውለናል።
ይሁንና የሁነቱ ትክክለኛ አውድ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢዝነስ ዪኒቶች አንዱ በሆነውና በአየር መንገዱ ባለቤትነት ከሚተዳደረው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል መካከል የተደረገ ስምምነት ብቻ ሲሆን ይህም ታማኝ ግብር ከፋዮች የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ለደንበኞቹ በሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ለታማኝ ግብር ከፋይነታቸው የሚመጥን ልዩ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የጋራ መግባባት ከመደረሱ ውጪ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ ጋር የተደረገ ሌላ ሰምምነት አለመኖሩን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል

👍92❤23🎉2
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ ማህማትን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀብለን በክብር አስተናግደናል። ክቡር ሊቀ መንበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቅጥር ግቢ እና የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከፍተኛ የአመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታና ስኬት ጋር ቅርብ ቁርኝት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በምስረታው ወቅት የህብረቱ መስራች የነበሩ ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎችን ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በማጓጓዝ የተጫወተውን ቁልፍ ሚና ዛሬም አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር ይበልጥ በማስተሳሰር አይተኬ ሚናውን በትጋት እንደሚወጣ ይገልፃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ

👍27❤11