የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ የሚያደርጋቸው በረራዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስምረውበታል።
አየር መንገዳችን አሁን ላይ ወደ ሉሳካ 11 እንዲሁም ወደንዶላ በሳምንት 5 ጊዜ በመብረር ላይ ሲገኝ፤ በቅርቡም ወደ ንዶላ የሚደረገውን በረራ ወደ 7 ከፍ በማድረግ ወደ ዛምቢያ የሚደረጉትን አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራዎች 18 የሚያደርስ ይሆናል።

👍64❤33
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 78ኛ ዓመት መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በልዩ ድምቀት አከበረ። በዝግጅቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊው አየር መንገዱ ከ78 ዓመት በፊት የመጀመሪያ በረራውን ወዳደረገባት የካይሮ በረራ ላይ የተገኙ ሲሆን ለመንገደኞች አገልግሎት በማቅረብ ደንበኛን በትህትና በማገለገል የአመራር ተምሳሌት መሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱም ብሔራዊ አየር መንገዱ በጾም ላይ ላሉ ክቡራን መንገደኞቹ መልካም የጥሞና ግዜን ለመመኘት ያዘጋጀውን ስጦታ በተርሚናሉ ውስጥ አበርክቷል።
በዕለቱም ብሔራዊ አየር መንገዱ በጾም ላይ ላሉ ክቡራን መንገደኞቹ መልካም የጥሞና ግዜን ለመመኘት ያዘጋጀውን ስጦታ በተርሚናሉ ውስጥ አበርክቷል።
❤89👍47👏9🥰8🎉8😍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለ 78 ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ አመራር እና ትጋት የተሞላበት አገልግሎት! #የኢትዮጵያአየርመንገድ #78ስኬታማአመታት
❤110👍17👏12🥰10😍2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን ዓለም-አቀፍ በረራ ያደረገው ከ78 ዓመታት በፊት መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ወደ ግብፅ ካይሮ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ጊዜያት የገጠሙትን ፈተናዎች በስኬት በማለፍ ዛሬ ላይ በአፍሪካ እጅግ ግዙፍ፣ ትርፋማ እና የበርካታ ዓለም-አቀፍ የአቪዬሽን ሽልማቶች ባለቤት ለመሆን በቅቷል። አየር መንገዳችን በዓለም ተወዳዳሪ ከሚባሉ ቀዳሚ አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉ የስኬት ተምሳሌት እንዲሆን አስችሎታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #78ስኬታማአመታት #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #78ስኬታማአመታት #ትውስታ
❤110👍35👏9🎉9🥰5