Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ-ስረዓት አስመረቀ። በ3500 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ መሰረተ ልማት ወደ ከተማዋ የሚጓዙ መንገደኞችን ምቾት ከፍ የሚያደርግና የአካባቢውን የቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ መልኩ የሚያግዝ ነው። ውድ ክቡራን መንገደኞቻችን ወደየትኛውም የዓለም ጫፍ ጉዞዎን ማድረግ ሲያሻዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ትኬት ቢሮ በአካል በመሄድ አልያም የሞባይል መተግበሪያችንን ወይም ድረገጻችንን በመጠቀም ትኬትዎን ገዝተው የማይረሳ ጉዞ ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
63👍49👏19🎉9😍6
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
96👍19
ያልተቆጠበ አገልግሎት!
👍12085🥰23🎉14👏12
ከልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ጋር አይረሴ ጉዞዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
95👍44🥰18😍2
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
68👍24👏11🥰7
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ የሚያደርጋቸው በረራዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስምረውበታል።
አየር መንገዳችን አሁን ላይ ወደ ሉሳካ 11 እንዲሁም ወደንዶላ በሳምንት 5 ጊዜ በመብረር ላይ ሲገኝ፤ በቅርቡም ወደ ንዶላ የሚደረገውን በረራ ወደ 7 ከፍ በማድረግ ወደ ዛምቢያ የሚደረጉትን አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራዎች 18 የሚያደርስ ይሆናል።
👍6433
ብቃት ባላቸው ባለሞያዎቻችን ታግዘን ካሰቡበት ቦታ ልናደርስዎ ተዘጋጅተናል፣ ይምጡ አብረውን ይጓዙ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
170👍50👏13🎉8😍5
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 78ኛ ዓመት መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በልዩ ድምቀት አከበረ። በዝግጅቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊው አየር መንገዱ ከ78 ዓመት በፊት የመጀመሪያ በረራውን ወዳደረገባት የካይሮ በረራ ላይ የተገኙ ሲሆን ለመንገደኞች አገልግሎት በማቅረብ ደንበኛን በትህትና በማገለገል የአመራር ተምሳሌት መሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱም ብሔራዊ አየር መንገዱ በጾም ላይ ላሉ ክቡራን መንገደኞቹ መልካም የጥሞና ግዜን ለመመኘት ያዘጋጀውን ስጦታ በተርሚናሉ ውስጥ አበርክቷል።
89👍47👏9🥰8🎉8😍2
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባት አሥርት ዓመታት በላይ በነበረው ጉዞው ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል ያስቻለው የማይለዋወጥ ወጥ አቋም በመያዝ በትጋት በመሥራቱ ሲሆን ይህን እድገትን ለማስቀጠል የደንበኞች አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ነው።”

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ
100👍45👏21🥰6🎉3😍1