Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የዚህን አውሮፕላን ዓይነት ይገምቱ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍18869🥰16😍16
የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት ጀመረ።
አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳደገ።
አዲሱን በረራ አስመልክቶ የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡ “ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ በረራ የሰሜን አፍሪካን የመግሪብ ቀጠና ወደ ዓለም-አቀፉ የጭነት አገልግሎት መዳረሻዎቻችን ያካተተ በመሆኑ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሆኗል። የዚህ በረራ መጀመር በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ የዓለም ንግድ እና ሸቀጦች ፍሰትን ለማሳለጥ አዳዲስ የጭነት መስመሮችን በመክፈት አገልግሎቱን በዓለም ዙሪያ ማስፋፋቱን ይቀጥላል። ወደ ካዛብላንካ የምናደርገው የጭነት በረራ በዘመናዊው እና ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን የሚደረግ ይሆናል።” #የኢትዮጵያአየርመንገድ
94👍84😍10🥰7👏5🎉1
በአፍሪካ አንጋፋ እና ግዙፍ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 135 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ ከ147 በላይ የሆኑ ዘመናዊ አውሮፕላኖቹን በመጠቀም ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት ዓለም-አቀፍ ዕውቅና በተቸረው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ የላቀ የበረራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
101👍36👏16
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፍቅረኞች ቀንን በማስመልከት ከአዲስ አበባ ሞምባሳ፣ ኖሲ ቤ፣ ሲሺየልሽ እና ባንኮክ ከተሞች የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቶ እንደሚጠብቅዎ ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል።ትኬትዎን ከጥር 6 ቀን እስከ ጥር 16 ቀን 2016 ዓ. ም ይግዙ፤ጉዞዎን ከየካቲት 3 ቀን እስከ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ. ም ያድርጉ። አንድ ትኬት ሲገዙ አንድ ትኬት በነፃ ይሸለማሉ። ለተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽያጭ ቢሮ አሊያም የጉዞ ወኪልዎን እንዲሁም ድረ ገፃችንን www.ethiopianairlines.com ይጎብኙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍8334👏12🎉12
በአውሮፕላን ሲጓዙ የመቀመጫ ወንበር ምርጫዎ የቱ ጋር ነው? በመስኮት በኩል ልብን በሐሴት በሚሞሉ ዕይታዎች እየተደመሙ? እግርዎን ዘርግተው ዘና ለማለት በሚመቸው የፊት ወንበር? ወይንስ ለእንቅስቃሴ በሚመችዎት የመተላለፊያ ዳር? ምርጫዎን ያሳውቁን፤ ምቾትዎን ለመጠበቅ ሁሌም እንተጋለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
106👍46👏13
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ኤሮ ክለብ በአቪዬሽን መስክ በጋራ ብቁ እና የሰለጠነ  የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
👏7641👍34😍5🎉3
ዓለም-አቀፍ እውቅና ባተረፈው መስተንግዷችን እናገለግልዎታለን! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
140👍52🥰12👏6
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
162👍45👏24🥰18🎉18
#ከኢትዮጵያአየርመንገድ ጋር በምቾት ይጓዙ።
104👍38🎉14😍7
ከእኛ ጋር ወደሚፈልጉት መዳረሻ ለመብረር ይዘጋጁ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
96👍35🥰11👏9🎉5
ማሳሰቢያ

ከዚህ በፊት አጭበርባሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ጭነት አገልግሎት (ካርጎ) በኩል ለተለያዩ ግለሰቦች ዕቃ እንደተላከላቸው አስመስሎ በመደወል እና ሐሰተኛ የእቃ ጭነት መለያ ቁጥር Air Waybill (AWB) በመጠቀም የተላከውን ዕቃ ለመቀበል የሚከፈል በሚል ክፍያ በመጠየቅ እንዲሁም ስራ ፈላጊዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመቀጠር ለምዝገባ እና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል ገንዘብ በማስከፈል የማታለል ተግባር ላይ መሰማራታቸውንና ማሕበረሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባችን ይታወቃል፡፡

በቅርቡም የካናዳ መንግስት የስራ እና የትምህርት እድል እንዳወጣ እና ተቋማችን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሰው እንደወከለ እንዲሁም መመዝገብ ለሚፈልጉም ሁሉ ክፍያ የሚፈፅሙበት የባንክ አካውንትም አንዳሳወቀ በማስመሰል ደብዳቤ በማዘጋጀት ሰዎችን የማታለል ተግባር ላይ አጭበርባሪዎች መሰማራታቸውን ደርሰንበታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ለተላከላቸው ደንበኞቹ ዕቃቸው መድረሱን እና ወደ ድርጅቱ በመምጣት አስፈላጊ ሂደቶችን እንዲያስጀምሩ ከማሳወቅ ውጪ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዲከፍሉ በስልክ የማይጠይቅ መሆኑን፣ ለስራ ቅጥር ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ እና ከማንኛውም አይነት ኤጀንት ጋር አብሮ የማይሰራ መሆኑን እና ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ የትኛውም ሀገር ሰዎችን የመላክ ስራ ላይ እንዳልተሰማራ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

ስለሆነም ማሕበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማሳሰብ እንወዳለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍10729👏12
የዛሬውን ምስል ያጋሩን Ethiopian Airlines Fanpage ናቸው፤ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍13739🥰12👏9🎉1
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ። #ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍7147🥰8
በዛሬው ዕለት ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ በበረራ ቁጥር ET106 የተደረገው በረራ በኤርፖርቱ ካረፈ በኋላ ከበረራ መስመር የመንሸራተት ችግር ገጥሞታል።
ሁሉም የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች እንዲሁም የበረራ ባለሙያዎች ያለምንም ጉዳት ከአውሮፕላኑ ወጥተዋል።
የችግሩን መነሻ አየር መንገዳችን በማጣራት ላይ ይገኛል።
በዚሁ አጋጣሚ ክቡራን ደንበኞቻችን ላይ በደረሰው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍21265👏26🎉12🥰6