Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.58K photos
134 videos
2 files
399 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ለሚያደርጉት በረራ ልዩ ቅናሽ አዘጋጅቶ እንደሚጠብቅዎ ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል። ትኬትዎን እስከ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ይግዙ ፤ በረራዎን እስከ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ያድርጉ ። ለተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽያጭ ቢሮ አሊያም የጉዞ ወኪልዎን ይጎብኙ። እንዲሁም ድረ ገፃችንን www.ethiopianairlines.com ይጎብኙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Fahima Mohamed ናቸው፤ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ዳሸን ባንክ ደንበኞች የድህረ-ጉዞ ክፍያ መፈጸም የሚችሉበትን አዲስ የክፍያ አማራጭ በጋራ አስተዋወቁ።
መልካም በረራ የስታር አሊያንስ አባል በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ!
የስኬት ጉዞዎን አስደሳች በሆነው መስተንግዷችን እናጅባለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወዳሰቡት መዳረሻ ልናደርስዎ ሁልጊዜ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ ቶሮንቶ ካናዳ የምናደርገው በረራችንን ከመጋቢት 23, 2016 ጀምሮ ወደ ዕለታዊ ማሳደጋችንን ስንገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ከታኃሣሥ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Eben Ezer ናቸው፤ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ። #ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ሞምባሳ ፣ ኖሲ ቤ እና ሲሺየልሽ ከተሞች የእረፍት ቀናት የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል። ትኬትዎን ከታሕሳስ 29 እስከ ጥር 3 ቀን 2016 ዓ. ም ይግዙ፤ጉዞዎን ከጥር 8 ቀን እስከ ጥር 14 ቀን 2016 ዓ. ም ያድርጉ። አንድ ትኬት ሲገዙ አንድ ትኬት በነፃ ይሸለማሉ። ለተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽያጭ ቢሮ አሊያም የጉዞ ወኪልዎን ይጎብኙ። እንዲሁም ድረ ገፃችንን www.ethiopianairlines.com ይጎብኙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዓለም-አቀፍ ምርጥ መስተንግዷችንን ከደማቅ ፈገግታ ጋር አጅበን የበዓል ወቅት ጉዞዎን እናሳምራለን! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዚህን አውሮፕላን ዓይነት ይገምቱ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት ጀመረ።
አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳደገ።
አዲሱን በረራ አስመልክቶ የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡ “ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ በረራ የሰሜን አፍሪካን የመግሪብ ቀጠና ወደ ዓለም-አቀፉ የጭነት አገልግሎት መዳረሻዎቻችን ያካተተ በመሆኑ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሆኗል። የዚህ በረራ መጀመር በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ የዓለም ንግድ እና ሸቀጦች ፍሰትን ለማሳለጥ አዳዲስ የጭነት መስመሮችን በመክፈት አገልግሎቱን በዓለም ዙሪያ ማስፋፋቱን ይቀጥላል። ወደ ካዛብላንካ የምናደርገው የጭነት በረራ በዘመናዊው እና ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን የሚደረግ ይሆናል።” #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አንጋፋ እና ግዙፍ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 135 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ ከ147 በላይ የሆኑ ዘመናዊ አውሮፕላኖቹን በመጠቀም ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት ዓለም-አቀፍ ዕውቅና በተቸረው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ የላቀ የበረራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ