Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማድሪድ የሚያደርገውን በረራ በደማቅ ስነ-ስርዓት በይፋ አስመጀረ። በረራውም በሳምንት አራት ቀናት የሚደረግ ይሆናል።
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ 627 የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ!
• 88 አብራሪዎች፣
• 125 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች፣
• 150 የበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎች እና
• 264 የትኬት ሽያጭ እና የደንበኛ አገልግሎት ባለሙያዎችን
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርሲቲ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። መልካም ቀን ይሁንልዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ምቹ እና አስደሳች የበረራ ጊዜ ያሳልፉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች እና የማይረሳ ጉዞ ከእኛ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ

ከዚህ በፊት አጭበርባሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ጭነት አገልግሎት (ካርጎ) በኩል ለተለያዩ ግለሰቦች ዕቃ እንደተላከላቸው አስመስሎ በመደወል እና ሐሰተኛ የእቃ ጭነት መለያ ቁጥር Air Waybill (AWB) በመጠቀም የተላከውን ዕቃ ለመቀበል የሚከፈል በሚል ክፍያ በመጠየቅ እንዲሁም ስራ ፈላጊዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመቀጠር ለምዝገባ እና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል ገንዘብ በማስከፈል የማታለል ተግባር ላይ መሰማራታቸውንና ማሕበረሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባችን ይታወቃል፡፡

በቅርቡም የካናዳ መንግስት የስራ እና የትምህርት እድል እንዳወጣ እና ተቋማችን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሰው እንደወከለ እንዲሁም መመዝገብ ለሚፈልጉም ሁሉ ክፍያ የሚፈፅሙበት የባንክ አካውንትም አንዳሳወቀ በማስመሰል ደብዳቤ በማዘጋጀት ሰዎችን የማታለል ተግባር ላይ አጭበርባሪዎች መሰማራታቸውን ደርሰንበታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ለተላከላቸው ደንበኞቹ ዕቃቸው መድረሱን እና ወደ ድርጅቱ በመምጣት አስፈላጊ ሂደቶችን እንዲያስጀምሩ ከማሳወቅ ውጪ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዲከፍሉ በስልክ የማይጠይቅ መሆኑን፣ ለስራ ቅጥር ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ እና ከማንኛውም አይነት ኤጀንት ጋር አብሮ የማይሰራ መሆኑን እና ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ የትኛውም ሀገር ሰዎችን የመላክ ስራ ላይ እንዳልተሰማራ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

ስለሆነም ማሕበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማሳሰብ እንወዳለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲን ተቀላቅለው ህልምዎን ያሳኩ!
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርሲቲ
ከአፍሪካ ኩራት ጋር ከፍ ብለን እንብረር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንጊዜም ለመንገደኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ይተጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምርጫዎን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድን
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል በረራ የጀመረበትን 40ኛ ዓመት በድምቀት አከበረ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ