የእንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል ክብርት ሶፊ ሄሌን ራይስ ጆንስ ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርና በአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልእክተኛ ዳረን ዌልች እና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ አመራር አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ማጠቃለያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራ ማድረግ የጀመረበት 50ኛ ዓመት በኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርስቲ ተከብሯል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጅስቲክስ አገልግሎት በአረቢያን የጭነት ሽልማት ውድድር በሶስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። ዘርፎቹም በፍጥነት እያደገ ያለ ዓለም አቀፍ የጭነት አየር መንገድ ፣ ምርጥ የህክምና ቁሳቁሶች ጭነት አየር መንገድ እና በአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ ናቸው። ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስቱ ዘርፎች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድምፅዎን ይስጡ።
https://rb.gy/m3tue
https://rb.gy/m3tue
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ ዕይታ ያጋሩን ጋሬብ አሕመድ ናቸው እናመሰግናለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET-ABY ዳግላስ አውሮፕላን ሚያዝያ 16 ቀን 1965 ዓ.ም ለመጀመሪያ የበረራ ደህንነት ፍተሻ ወደ ጥገና ክፍል ሲገባ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲሺየልስ ከሚያደርገው እለታዊ በረራ በተጨማሪ ከጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አራት ሳምንታዊ የማለዳ በረራዎችን በመጀመር አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራውን ወደ 11 ከፍ እንደሚያደርግ ሲገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች ዜና!
ኅዳር 11 ወደ ለንደን ጋትዊክ ኤርፖርት በምንጀምረው የመክፈቻ በረራ ላይ ይታደሙ፤ ተጨማሪ አንድ ሻንጣ የመያዝ እና የ3651 ማይልስ ቦነስ ያጣጥሙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ኅዳር 11 ወደ ለንደን ጋትዊክ ኤርፖርት በምንጀምረው የመክፈቻ በረራ ላይ ይታደሙ፤ ተጨማሪ አንድ ሻንጣ የመያዝ እና የ3651 ማይልስ ቦነስ ያጣጥሙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ