Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.77K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ምቾትዎን ጠብቀን እርስዎን በብቃት ማገልገላችን የሁልግዜም ኩራታችን ነው! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቱሪዝም ዘርፍ የላቀ ሚና ለተጫወቱ የጉዞ ወኪሎች የዕውቅና ሽልማት ሰጠ፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቱሪዝም
የመልካም ሳምንት መልዕክት ለሁላችሁም!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በፈገግታ ታጅበዉ ከእኛ ጋር ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ መሆናቸውን ለክቡራን ደንበኞቹ ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጣችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን ትኬታችሁ ለአንድ ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቃችሁ ወደፊት በፈለጋችሁት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር የምትችሉ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆንላችሁ የምትፈልጉ ክቡራን ደንበኞቻችን አቅራቢያችሁ ወዳሉ የአየር መንገዱ የትኬት መሸጫ ቢሮዎች ወይንም የጉዞ ወኪሎቻችሁ በመቅረብ መስተናገድ እንደምትችሉ በትህትና እንገልጻለን፡፡
አየር መንገዱ በዚህ ረገድ ለሚፈጠረው መጉላላት ልባዊ ይቅርታውን ያቀርባል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!
ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም.
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እየገለጸ፣ ክቡራን መንገደኞቻችን በአቅራቢያችሁ በሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከላችን (6787/+251116179900) በመደወል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!
ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም.
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በልዩ ልዩ የአቪዬሽን ዘርፎች የወጣ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ! https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies
አብራሪዎች የቅድመ በረራ ፍተሻ በማድረግ ላይ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እየገለጸ፣ ክቡራን መንገደኞቻችን እንደተለመደው ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቻችንን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟችሁ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ዕገዛ የምትሹ መንገደኞቻችን በአቅራቢያችሁ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከላችን (6787) በመደወል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!

ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም.

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደሚወዱት መዳረሻዎ ልናደርስዎ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እየገለጸ፣ ክቡራን መንገደኞቻችን እንደተለመደው ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቻችንን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟችሁ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ዕገዛ የምትሹ መንገደኞቻችን በአቅራቢያችሁ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከላችን (6787) በመደወል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!

የክቡራን መንገደኞቻችንን ፍላጎት በማጤን በድጋሚ ወደከፈትናቸው የአገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የበረራ ምልልሶቻችንን ለመጨመር ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡


ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም.
#የኢትዮጵያአየርመንገድ