የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አየር መንገዱ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳትፎውን ቀጥሏል።እንደባለፈው አመት በዘንድሮ የክረምት ወቅትም 100 ሺህ ችግኞችን በተለያዩ ሥፍራዎች ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል።በዚህም የአየር መንገዱ አመራሮች ፣ሠራተኞች እና የቦርዱ አባላት በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በመገኘት ከከተማው ፣ከክፍለ ከተማው እና ከወረዳው አመራር ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን ተናግረዋል። የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ። ትኬትዎን በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ችን ቆርጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ያግኙ። https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ