በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ የነበራቸውን ቆይታ በማራኪ ምስል ያጋሩን @MariaAklilu ናቸው እናመሰግናለን። እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ የነበርዎትን ቆይታ በመልዕክት ሳጥን መቀበያ ይላኩልን ፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍68🥰19❤16👏7
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ካምፓኒ ጋር በመተባበር ከ12,000 ፓውንድ በላይ የሚመዝኑ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በቅርቡ በተረከባቸው ሶስት አዲስ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ አጓጓዘ። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3P74KlL
❤49👍37🥰5🎉5
ለየብስ ትራንስፖርትዎ ሁነኛ አማራጭ አዘጋጅተናል! በመዳረሻዎ ያለ ሃሳብ እንዲንቀሳቀሱ ተሽከርካሪ መከራየት እና፣ወይም ከአየር ማረፍያ የየብስ መጓጓዣ አገልግሉት እና ተሽከርካሪ ከነሹፌሩ መከራየት የሚችሉበትን አማራጭ አመቻችተናል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ። https://bit.ly/3uxfEaH
👍41❤20👏6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ለ "Top Shop Awards 2023" ሽልማት በእጩነት ቀርቧል። በአፍሪካ የአውሮፕላን ጥገና መስክ ቀዳሚና በአለም ተመራጭ ከሆኑት የጥገና ማዕከላት አንዱ ለሆነው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ድምፅዎን ይስጡ። https://bit.ly/3Hod5zo
👏97👍47❤31🎉10🥰9
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካው “Global Traveller” መፅሔት ከመንገደኞች በሚያሰባስበው ድምፅ መሰረት በሚያበረክተው የእውቅና ሽልማት “የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።
https://bit.ly/3uO0uOF
https://bit.ly/3uO0uOF
👏98👍49❤13🎉12🥰2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በመጪው የካቲት ወር በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በሚካሄደው “The STAT Times International Award for Excellence in Air Cargo” ውድድር ላይ በምርጥ የአመቱ የአፍሪካ ካርጎ ኤርፖርት፣ የአመቱ ፈጣን እድገት ያስመዘገበ ዓለም ዓቀፍ ካርጎ አገልግሎት ፣ የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ እና ዘላቂና አስተማማኝ የካርጎ አገልግሎት አመራር ዘርፎች ይወዳደራል። ከታች ባለው ሊንክ እስከ ጥር 7 2015 ዓ.ም በአራቱ ዘርፎች ድምፅዎን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ይስጡ።
https://www.stattimes.com/air-cargo-africa-2023/nominations
https://www.stattimes.com/air-cargo-africa-2023/nominations
❤79👍64🥰13👏12
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ ነገ ታሕሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቹ እየገለፀ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ በመጠቀም የበረራ ትኬት መግዛት የሚችሉ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
❤101👍59👏10🥰8😍8🎉7