የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማሕበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት በማጠናከር ከጤና ሚኒስቴር ፣በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕፃናት መርጃ እና ከሮተሪ ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። በስምምነቱ መሰረት አየር መንገዳችን በህንድ ሀገር የልብ ህመም ህክምና ለማግኘት የሚሔዱ አንድ መቶ ሕፃናት እና ከሕፃናቱ ጋር አብረው ለሚጓዙ አንድ መቶ ቤተሰቦቻቸው የአየር ትራንስፓርት ወጪ የሚሸፍን ይሆናል።
👍5
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የ “Air Cargo Industry Customer Care” ሽልማት አሸናፊ እንዲሆን ድምፃችሁን ለሰጣች ሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን ወደ ግሪክ አቴንስ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ከ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቀጥል ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል። በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን ወይም በድረ ገፃችን ተጠቅመው ትኬትዎን ይግዙ ። መልካም በረራ !
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍4❤3
ካፒቴን መኮንን በሪ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ 1958 ዓ.ም ወደ ጃማይካ ያደረጉትን ታሪካዊ በረራ በዋና አብራሪነት የመሩ አንጋፋ ካፒቴን ሲሆኑ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ታሪክ ዙሪያ የመጀመሪያ ነው የሚባለውን “አቪዬሽን በኢትዮጵያ” የተሰኘውን መፅሐፍም ፅፈው ለህትመት አብቅተዋል።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍16
በእድሳት ላይ የነበረው የዱባይ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሰሜናዊ ክፍል እድሳቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት በመደረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሶስት እለታዊ በረራዎቹን ከዱባይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (DXB) ተርሚናል 1 እንደሚያደርግ በደስታ ይገልፃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍3❤2
የሲሺየልስ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዋቭል ራምካላዋን እና ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ወ/ሮ ሊንዳ ራምካላዋን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመብረራቸውና ተቀብለን በማስተናገዳችን ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍5❤1🥰1