Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.7K subscribers
3.83K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
መድረሻዎን ይወስኑ፣ አብረውን ይጓዙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በስኬት ከፍታ ልቆ የሚታይ !#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍2
የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/,የአውሮፓ ህብረት አቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/, CAAC, ECAA እንዲሁም ሌሎች በርካታ የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ጥልቅ ምርመራና ፍተሻ ካደረጉና ዳግም ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ የማክስ አውሮፕላናችንን ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውናል፡፡ ለደህንነት ቅድሚያ እንደመስጠታችንና ማክስ አውሮፕላንን ወደ ስራ ለመመለስ ከመጨረሻዎቹ አየር መንገዶች ተርታ እንደምንሆን በገባነው ቃል መሰረት እስካሁን 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደበረራ በመመለስ ከ330 ሺህ በላይ በረራዎችን አድርገዋል፡፡ የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ መሃንዲሶች፣ የአውሮፕላን ጥገና ባለሞያዎች እንዲሁም የበረራ አስተናጋጆች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻችንን ወደ በረራ ለመመለስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተዋል፡፡ ከእኛ ጋር አብረውን እንዲበሩ ተጋብዘዋል፤ ለበረራው ሲመጡ እርስዎን ሞቅ ባለ አቀባበል ለመቀበል ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
ለ 75አመታት አፍሪካውያንን እርስ በርስ እያስተሳሰረ እንዲሁም ከተቀረው አለም እያገናኘ ያለውና የአፍሪካ ምልክት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡ ተሳታፊዎች እስከ 15 በመቶ የሚደርስ የጉዞ ትኬት ዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል! ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ላይ መስተንግዶ ባልደረቦቻችን በዘመን #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን በረራ ወደ ዱባይ እንደሚጀምር ሲገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።
የጉዞ ምዝገባዎን ለመያዝ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
ከእኛ ጋር ስለበረሩ እናመሰግናለን! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ፓን አፍሪካዊ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ መለያ አርማ ሆኖ ላለፉት 75 ዓመታት አፍሪካውያንን እርስ በርስ እያስተሳሰረ ዘልቋል። ይሕን አጭር ቪዲዮ እንዲመለከቱ ጋብዘንዎታል! https://youtu.be/5vZ42XGIVlQ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጉዞዎን ቀላል እና ምቹ ያድርጉ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
www.ethiopianairlines.com/et
አገልግሎታችንን አስፍተን ወደ 127 መዳረሻዎቻችን በከፍታ እንበራለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ ታላቁና የአህጉሪቱ የአቪየሽን መሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑን ዛሬ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዳግም ወደ አየር መለሰ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአየር መንገዱ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦይንግ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞችና ደንበኞች በዚህ የመጀመሪያ በረራ ላይ ታድመዋል።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ አገልግሎት መመለስ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ “የበረራ ደህንነት የአየር መንገዳችን ተቀዳሚና ወሳኝ ጉዳይ ነው፤ እያንዳንዷ የምንሰራት ስራና የምንወስናት ውሳኔ በበረራ ደህንነት አብይ ጉዳይ የተቃኘ ነው። በዚህ መርህ ላይ በመመስረት ነው ዛሬ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላናችንን ወደ አገልግሎት የመለስነው።" ብለዋል።
የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/፣ የአውሮፓ ህብረት የአቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/፣ ትራንስፖርት ካናዳ፣ የቻይና ሲቪል አቪየሽን አስተዳደር /CAAC/፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን /ECAA/ እንዲሁም ሌሎች የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት ለአውሮፕላኑ ምስክርነትና ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆን፣ 36 የሚሆኑ የአለም አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት መልሰዋል። የማክስ አውሮፕላን ሞዴል ዳግም ወደበረራ ከተመለሰበት አንድ ዓመት ወዲህ በአጠቃላይ 349 ሺህ በረራዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም ወደ 9መቶ ሺህ የሚደርስ የበረራ ሰአት አስመዝግቧል።
👍21
ትውስታ ከካፒቴን አዳሙ መድሀኔ ጋር። #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ አገልግሎት የተመለሰበት የመጀመሪያ በረራ በእሁድን በኢቢኤስ @EBStv #የኢትዮጵያአየርመንገድ https://www.youtube.com/watch?v=aC8MfFsTRZg
ሳምንትዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይጀምሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 joaquinspotter