Dagmawi Babi
6.44K subscribers
14.8K photos
1.96K videos
232 files
2.07K links
Believer of Christ | Creative Developer.

Files Channel: https://t.me/+OZ9Ul_rSBAQ0MjNk

Community: @DagmawiBabiChat
Download Telegram
እንኳን ደህና መጣሽ

"እንኳን ደህና መጣሽ?" ሲለኝ
ሰማሁና ደነገጥኩኝ
መቆሸሼ መበደሌ እየተሰማኝ
ወደ ኋላ አፈገፈግሁኝ፡፡
ገና ከመግባቴ አንስቶ
መንቀርፈፌን ተመልክቶ
ወደ እኔ ጠጋ አለና
በጥያቄም በልመና
"የሚጎድልሽ ይኖር ይሆን?"
ከእኔ ጠበቀ ምላሼን፡፡
"እንግዳ ነኝ" ብዬ አልኩኝ
"እዚህ መሆን 'ማይገባኝ"
እርሱ ግን. . .
ለስለስ አድርጎ ድምፁን
"እዚህ ሥፍራ - ግብዣ ቢኖር - ልዩ ክብር
ዋና እንግዳ - ተጋባዡ - አንቺ ብቻ - ትሆኝ ነበር!"
ሲለኝ ሰውነቴን አደረገው ውርር፡፡
" እኔ ኃጢአተኛ - ውለታ ቢስ የሆንኩኝ ሰው?
አንተን ማየት እንኳን የማልችለው?" - ስለው
"ዓይንን የሰጠ የተከለው
ከእኔ በቀር እስኪ ማነው?"
"እውነት ነው ጌታ ሆይ...
የእኔን ዓይኖች ግን ብታይ
አጥፍቻቸዋለሁ. . .
የሚያሳፍር ሥራ ሠርቻለሁ
የሚገባኝን ልቀበል . . .
ላከኝ ልሂድ ወደ ሲዖል"
ስለው እጄን ያዝ አድርጎ
ፊቱ በርቶ አፈግጎ...
"አላወቅሽም ይሆን? ያረኩልሽ ምን እንደሆን?
ተሸክሜ በደልሽን ተቀብዬ ኃላፊነቱን
በመስቀል ላይ መሰቀሌን... እንዳስተናግድሽ አሁን?
አረፍ በይ ተረጋጊ ...
ማዕዱንም ጠጋ አድርጊ"
ሲለኝ እኔም እፎይ አልኩኝ
ከገበታው ተመገብኩኝ!

#Poems #EnkuanDehnaMetash
@Dagmawi_Babi