ከተረጂነት እሳቤ መላቀቅ አለብን የአሜሪካ እርዳታ ለጊዜው መቆሙን ተከትሎ የተሰጠ አስተያየት ነው።
#ኬንያ #Kenya 🇰🇪 ኬንያ ትመቸኛለች!
* አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በኤክስ ገፃቸው እንደፃፉት!...
#Ethiopia | የቀድሞው የኬንያ ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአሜሪካ መንግሥት ለአገራቸው ሲሰጥ የነበረውን ዕርዳታ በማቆሙ ላዘኑ ኬንያውያን የሰጡትን አስተያየት አድምጬ አስተሳሰባቸውን በጣም አደነቅሁ:-
"ለምንድን ነው እርዳታው በመቋረጡ የምትንጫጩት? አሜሪካ አገራችሁ አይደለም፣ የናንተ መንግሥት አይደለም፣ የአሜሪካ መንግሥት ለናንተ ርዳታ የሚሰጥበት ምንም ምክንያት የለውም፣ ለአሜሪካ ግብር አትከፍሉም፥ ርዳታው ቀድሞውንም ምክንያታዊ አይደለም፣ ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆነን ይገባል እንጂ ማለቃቀስ የለብንም፤ ስለዚህ ራሳችንን ለመርዳት ምን ማድረግ አለብን ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን፤ ሐብታችንን በአግባቡ ለመጠቀም የምናስብበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ሐብታችንን ለጠመንጃና ጥይት መግዣም አይደለም የምናውለው? ወንድም እህቶቹን፥ ወገኖቹን ለመግደል ለመገዳደል አይደለም የምንጠቀመው? ሐብታችንን ለጥፋት ዓላማ እያዋልን ገንዘብ ልመና ከምንዞር፣ ሲናጣ ከሚንጫጫ ፀጋዎቻችንን ለተገቢው ዓላማ ማዋል አለብን" ነው ያሉት።
ኡሁሩ እውነታቸውን ነው ያሉት። ጉዳዩ እኛንም ይመለከታል፣ መልዕክቱ ለእኛም ጭምር ያገለግላል። እንዲያውም ከኬንያ በላይ የተረጂነት በሽታ ያጠቃው እኛን ነው። ሳናጣ ያጣን፣ እያለን የደሀየን እንቆቅልሽ የሆንን ሕዝቦች ነን። ባልሠለጠነ የፖለቲካ ባሕላችን ምክንያት የሚከሰቱ ልዩነቶች ለሚያስከትሉት ጦርነቶች የምናውለው ህልቆ መሳፍርት ሐብት፣ የምናባክናው ጊዜ፣ የሚጠፋው አምራች የሰው ሐይል በአግባቡ ብንጠቀምበት የትና የት ባደረሰን ነበር።
በሥርቆት የሚናባክነው ሲጨመርበት ደግሞ...። አፍሪካውያን በሙሉ የዚህ የተረጂነትና የአባካኝነት በሽታ ተጠቂዎች ቢሆኑም የእኛ የኢትዮጵያውያን ግን የከፋ ነው። ስለዚህ የኡሁሩን የማንቂያ መልዕክት በፍጥነት መጠቀም ይኖርብናል።
https://t.me/AleHig
#ኬንያ #Kenya 🇰🇪 ኬንያ ትመቸኛለች!
ለምንድን ነው እርዳታው በመቋረጡ የምትንጫጩት?

👍37❤6👎1😁1