#Ale
በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ግዛት በሁለት ኢትዮጵያውያን ላይ በተፈፀመ ግድያ ተጠርጥሮ በሀገሪቱ ፖሊስ የሚፈለገውን በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነውን አቶ ዮሃንስ ነሲቡ በዛብህን ለአሜሪካ መንግስት አሳልፋ ለመስጠት ወሰነች።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለfbc እንዳስታወቀው፥ የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዲቪዥን በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት በሁለት ሰዎች ሞት እና በሁለት የጦር መሳሪያን ያለአግባብ በመጠቀም ወንጀሎች ግለሰቡ መጠርጠሩን እና አሁን ላይ በኢትዮጵያ እንደሚገኝ በመግለፅ ተላልፎ እንዲሰጥ ጠይቋል።
በኢትዮጵያ በኩል ጥያቄውን ለመቀበል የሚያስችል ማረጋገጫ ከአሜሪካ መንግስት በኩል እንዲሰጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የተከናወነው የወንጀል ምርመራ ውጤትን በሰነድ በማያያዝ አሜሪካ ማቅረቧን ነው ያመለከቱት። በሰነዱም ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቨርጂኒያ ግዛት ፌርፋክስ ካውንቲ ፍርድ ቤት ግለሰቡ መከሰሱን እና በፈረንጆቹ መጋቢት 23 ቀን 2017 የእስር ትእዛዝ እንደወጣበት አረጋግጧል።
በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 6 ንዑስ ቁጥር 12 በወንጀል ጉዳዮች ላይ ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ትብብር እንዲያደርግ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ተጠርጣሪው ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት መወሰኑን አቶ ዝናቡ አስታውቀዋል። ተላልፎ እንዲሰጥ ሲወሰንም ተፈላጊው ግለሰብ ዜግነቱ አሜሪካዊ መሆኑ እና ግድያ የተፈፀመባቸው ሁለቱ ሰዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት መሆኑ ተመልክቷል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሰረት የተፈፀመውን ወንጀል የመዳኘት ስልጣን በዋናነት የኢትዮጵያ አለመሆኑ እና ግለሰቡ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ የሰብዓዊ መብቱ እንደሚጠበቅ ከአሜሪካ በኩል ማረጋገጫ መሰጠቱ ከግንዛቤ ተወስዷል።
እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል ተመሳሳይ የትብብር ጥያቄ ለአሜሪካ ከቀረበ የጉዳዩን ይዘት በማየት ትብብር ከዋሽንግተን በኩል እንደሚደረግ ማረጋገጫ በመሰጠቱም ውሳኔው ተላልፏል ነው ያሉት። በሌላ በኩል በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል በፍትህ ዘርፍ እየተደረገ ያለው ግኑኝነት እና የትብብር መንፈስ አወንታዊ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ ግለሰቡ ተላልፎ እንዲሰጥ መወሰኑን አቶ ዝናቡ አስረድትዋል።
በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው ግለሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ አሳልፎ ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተሟሉ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
Via #FBC

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ያቀረባቸውን የቃል ምስክሮች በዛሬው ዕለት ማዳመጥ ጀምሯል።
ፍርድ ቤቱ ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ አሉኝ ያላቸውን የቃል ምስክሮች ከግንቦት 21 ጀምሮ እንዲያሠማ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
በዚህ መሰረትም በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው የቃል ምስክሮች በሁለቱ ተከሳሾች ላይ መስክረዋል።
Via #fbc

በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ8 ሺህ መብለጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
#CoronavirusAfrica : በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን 139 ሺህ መብለጡን የሚያሳየው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ ከእነዚህም ውስጥ 8 ሺህ 3ቱ በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ናቸው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ ሲበልጥ፤ በአፍሪካም በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ330 ተሻግሯል።
በአፍርካ ከ705 በላይ ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ማገገማቸውንም ነው የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያሚያመለክተው።
ከአፍሪካ አህጉር 1 ሺህ 505 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የያዘችው ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን፤ በሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ውስጥ የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 95 ሰዎች ማገገማቸውም ነው የተገለፀው።
በአልጄሪያም 1 ሺህ 171 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ 105 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ፤ 65 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
በግብፅም እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 985 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከእነዚህም 216 ሲያገግሙ፤ 66 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በሞሮኮም 858 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 62 ሰዎች ሲያገግሞ 50 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመጣ ኬንያ 122 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ያስታወቀች ሲሆን፥ ከእነዚህም 4 ሰዎች ሲያገድሙ፤ 4 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
በጂቡቲ 50 ሰዎች፣ በኤርትራ 22 ሰዎች፣ በሶማሊያ 7 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን እስካሁን የተመዘገበ ሞት የለም።
በኢትዮጵያም በዛሬው እለት ይፋ የተደረገውን ጨምሮ እስካሁን 38 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን፥ አራቱ ሲያገግሙ እስካሁም ሞት አልተመዘገበም።
Via #FBC
https://telegram.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/