አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ፕላስቲክ❗️ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፀደቀ!!

ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው #ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም መባሉን ሰምተናል፡፡

አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታን ያስቀምጣል፡፡አዋጁም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ምንጭ ፣ ሸገር ኤፍ ኤም