አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ እንዳለበት

በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677 መሠረት በቁ. 1845 ላይ የተቀመጠው #የ10_ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ ስለመሆኑ፣

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845   * ቅፅ-4 መ/ቁ 17937

ጋብቻ ልዩ ባህርይ ቢኖረውም ከሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት የሚመነጭ መብትና ግዴታም የሚጥል በመሆኑ በቤተሰብ ሕግ ግልጽ ድንጋጌ ሣይኖር ሲቀር በውል ሕግ መርሆች ወይም ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ የውል ሕግ አንቀጽ 1677ም የሚፈቅደው ነው:: ይኸው ድንጋጌ «ግዱታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች ይፈፀሙባቸዋል» በማለት ይደነግጋል፡፡ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተለየ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው በዚህ ድንጋጌ መሠረት የውል ሕግ የይርጋ ድንጋጌዎች እንዲገዛ ማድረግ ተገቢ ነው:: የውል ሕግ ይርጋ አጠቃላይ ድንጋጌ በአንቀፅ 1845 እንደተገለፀው በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር 10 ዓመት ነው፡፡

አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እና 1179/1/። ሰ/መ/ቁ-96628  ቅፅ-17.
በመሆኑም ፈቅዶ የሰጠው ሟች የቦታውን መብት ለባለ ሀብቱ እያስተላለፈ /እያጠ/ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ/826/2/ መሰረት አውራሻቸው የሌለው መብት ለወራሾች ሊተላለፍ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለም፡፡በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) መሠረት ባለመብት የሚሆነው አውራሽ ሳይቃወመው በራሱ ወጭ በሠራቸው ቤቶችና ቤቶቹ በተሰሩበት ወይም ባረፉበት ቦታ ላይ ብቻ ይሆናል ።ይህ ቦታም የውርስ ሀብት ክፍል በሆኑ ንብረቶቹ ውስጥ ሊካተት አይችልም ።
  #አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties