አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#የሙያ_ጥፋት_ምንድን_ነዉ?
(#Professional_Fault)

ሙያ የሚባለዉ ልዩ ስልጠና፣ልዩ ዕዉቀትና ችሎታ የሚጠይቅ የስራ መስክ ነዉ።ሙያ በከፍተኛ የትምህህርት ተቋማት ገብቶ በመማር የሚገኘዉን አንደሕክምናምህንድስና፣ሕግመምህርነት የመሳሰለዉን ሲሆን በስራ ላይ ባለሙያዎች የሚሰሩትን እያዩ ወይም አበሮ በመስራትም የሙያ ዕዉቀት በማግኘት ባሉያ መሆን ይቻላል።
አንድ ባለሙያ ሙያ ብቻ ሳይሆን የሙያዉን የስነ ምግባር ደንብ ጨምሮ ጠንቅቆ ማወቅና ኃላፊነቱን ከሙያዉ የስነ ምግባር ደንብ አንፃር በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል።የሙያ ጥፋት ብዙን ጊዜ የሚከሰተዉ ባለሙያዉ የሙያ ተግባሩን በሚፈጽመበት ጊዜ የሙያ ደንቦች ባለማክበሩ የሚከሰተ ጥፋት ነዉ
የሙያ ጥፋትን ፍትሐ ብሔር ሕጉ ምን ይላል?
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 መሰረት በለዩ ሙያዉ አንድ ስራ የሚፈፅም ሰዉ የሙያ ስራዉ የሚመራበትን ደንብ መጠበቅ እንደሚገባዉ የሕግ ግዴታ ተጥሎበታል።ይህ ባለሙያ በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች ሁሉ የሚያወቋቸዉን ደንቦች እና መመሪዎች ሳያከበር ቢቀር የሙያ ጥፋት ፈፀመ ይባላል። ለመሆኑ የሙያ ደንቦች
የሚባሉት የትኞቹናቸዉ?የሙያደንቦች በሕግ የተደነገጉወይም በሙያዉ የተሰማሩ ሰዎች አዉቀዉየሚገለገሉባቸዉ ከተለመዱ የመልካም አስራር መመሪያዎች የመነጩ ሊሆን ይችላል።
አንድ ባለሙያ የሙያ ደንቦችን ጣሰ የሚባለዉ መቼ ነዉ?ደንቦች በሕግ በግልፅ የታወጁ በሆነ ጊዜ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2035 መሰረት ባለሞያዉ በግልጽ የተመለከተዉን ደንበና ስርዓት የጣሰ እንደሆን ጥፋተኛ ነዉ
የሙያ ደንቦቹ በሕግ በግልፅ ያልተደነገጉ ሳይሆኑ ከተለመዱ የመልካም አሰራር መመሪያዎች የመነጨ በሆነ ግዜ የባለሙያዉ ተግባር ጥፋት የሚሆነዉ ሌላ ጥበብ ካለዉ አመዛዛኝ በሆነ ሰዉ አስራር የሚመራ ባለሙያ ጋር ሲነፃፀር ትክክል ሆኖ ያልተገኘ እነደሆነ ነዉ
የሙያ ደንቦች ሁሌም ቋሚ ናቸዉን?አንዳንድ ሙያዎቸ የሚተዳደሩት አንዴ በተወሰኑና በልማድ ላይ በተመሰረቱ ደንቦች ብቻ ሳይሆን በየጊዜዉ እያደገ እየተቀያየረ በሚሄድ በስነ ጥበብ ደንቦች ጭምር ነዉ።በመሆኑም አንድ ባለሙያ በየጊዜዉ እነዚህን ደንቦች የመመለከትና በሙያዉም የሚደረገዉን ምርምርና ለዉጥ ሁሉ የማወቅ ግዴታዉን መዘንጋት የለበትም።
አንድ ባለሙያ በዉል የገባዉን ግዴታ እንዴት ይወጣዋል? በመርህ ደረጃ አንድ ሰዉ በዉለ የገባዉን ግዴታ ካለተወጣ ከአላፊነት አያመልጥም።ነገር ግን በፍትሐ ብሔረ ሕግ ቁጭር 1795 መሰረት በዉል ግንኙነት በአንድ ሙያ የሚችለዉን ያህል በቻ ለማድረግ ዉል የገባዉ በሙያዉ ደንቦች መሰረት የተቻለዉን ሁሉ በሙሉ ኃላፊነትና በጥንቃቄ ካከናወነ አላፊነት የለበትም።ይህም ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመዉ የዕዉቀት ስራን በሚመለከቱ እንደ ሕክምና ባሉ ጉዳዮቸ ላይ ነዉ። ለምሳሌ አንድ ሐኪም በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2647 ድንጋጌ መሰረት በኪነ ጥበብ ደንቦች ጥፋት ካላደረገ በቀር ለመታከም ለተዋዋለዉ ሰዉ አላፊነት የለበትም። ነገር ግን በሙያዉ ኪነ ጥበብ ደንቦች መሰረት መስራት የሚገባዉን ሳይሰራ በመቅረቱ ወይም መስራት የማይገባዉን በመስራቱ ምከንያት የሕክምና አገልገሎት በሰጠዉ ሰዉ ላይ ጉዳት የሚያመጣ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ እንዲሁም ሕክምና ሊያደርግለት የተቀበለዉን ሰዉ በቂ ባልሆነ ምክንያት ሳይረዳዉ የቀረ እንደሆነ በሰራዉ ተጠያቂ ነዉ
በሙያ ስራ ሰለሚደረግ ጥፋትና የፍትሐ ብሔር ኃላፊነት፡ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2030 መሰረት አንደ ሰዉ ሕሊናን ወይም መልካም ጠባይን ተቃዋሚ በሆነ ዓይነት የማየገባዉን ስራ የሰራ ወይም የሚገባዉን ሳይሰራ የቀረ እንደሆነ ጥፋት አንደፈፀመ ይቆጠራል።
በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2031 መሰረት በልዩ ሙዉ አንድ ስራ የሚፈጽም ሰዉ በስነ ጥበብ ወይም ራሱ በሚሰራዉ ኪነ ጥበብ ደንቦች መሰረት ያሉበትን ግዴታዎች አለመከተሉ ሲገለጽ ባለመጠንቀቅ ወይም በቸልተኝነት ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ አላፊ/ተጠያቂ/ ይሆናል።
እንዲሁም ለመጉዳት በማሰብ እያወቀ በሌላ ሰዉ ላየ ከፍ ያለ ጉዳት ያደረሰ ሰዉ በሰራዉ ስራ የጠያቂ ነዉ
በሙያ ስራ ስለሚደረግ ጥፋትና የወንጀል አላፊነት፡ የወንጀል አላፊነት የሚኖረዉ በወንጀል ሕጉ እንዳይደረግ የተከለከለዉን በማድረግ ወይመ እንዲደረግ የታዘዘዉን ባለማድረግ ነዉ
በወንጀል ሕግ ቁጥር69 መሰረት የሞያ ገዴታን ለመወጣት የተፈጸሙ ደረጊቶች ከሙያዉ ደንብና አሰራር ልማድ ዉጭ ካልሆኑና በከባደ የሙያ ጥፋት ካልተፈጸሙ በቀር አያሰቀጡም ይላል።ከድንጋጌዉ መረዳት እንደሚቻለዉ በሙያ ስራ የሚፈጸም ድርጊት ጥፋት ወይም ቸልተኝነት ከሌለበት በቀር አያስቀጣም።
በወንጀል ሕግ ቁጥር 575 መሰረት ማንም ሰዉ የሞያ ግዴታን በመተላለፍ አስቦ በሰዉ አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል። ማንም ሰዉ በሕይወቱ፤ በሰዉነቱ፤ወይም በጤንነቱ ላይ ሊደርስ በሚችል ከባድ አደጋ ላይ የሚገኘዉን ሌላ ሰዉ ለመታደግ ወይም ለመርዳት የሙያ ግዴታ እያለበት ሊረዳዉ ሲችል አሰቦ ሳይረዳዉ የቀረ እንደሆነ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል።
ማንም ሰዉ የሌላ ሰዉን አካል ወይም ጤንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለበት በቸልተኝነት በሌላ ሰዉ አካል ወይም ጤንነት ላይ ጉዳተ ያደረሰ እንደሆነ በወንጀል ሕግ ቁጥር 559 መሰረት ተጠያቂ ይሆናል።
እንዲሁም የሌላ ሰዉን ሕይወት፤ጤንነት ወይም ደህንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለበት በቸልተኝነት ሰዉን የገደለ ሰዉ ቅጣቱ እንደሚከብድበት የወንጀል ሕግ ቁጥር 543(2) ይደነግጋል።
በሙያ ጥፋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ምን መብት አላቸዉ? ጉዳት የደረሰበት ሰዉ የባለሙያዉን አድራጎት ጥፋት መሆኑንና በዚህም የተነሳ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በማስረዳተ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2028 መሰረት ለደረሰበት ጉዳት ካሳ እንዲከፈል ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይቻላል። ነገር ግን ጉዳያቸዉን በራሳቸዉ ለመከታተል በአቅም ምከንያት የማይችሉ ዜጎች የአቅም ችገ ያለባቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ በመያዝ በጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ በዋናዉ መ/ቤትና በልደታ ወንጀል ዘርፍ እንዲሁም በአዲስ አበባ አሰሩም የጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ምድን ጽ/ቤቶች በመቅረብ ጉዳያቸዉን ዐቃቢ ህጎች እንዲከታተሉላቸዉ ማመልከት ይችላሉ። እንዲሁም የአቅም ሳይሆን የሕግ ዕዉቀት ችግር ያለባቸዉ ዜጎችም እንዲሁ ወደ ጽ/ቤቶች በመምጣት የምክር አገልግሎት በነጻ ማግኘት ይቻላል።
ሙያን አክበሮ መስራት የዜግነት ግዴታ ነው! ሃላፊነታችንን በያለንበት የሙያ መስክ በብቃት እንወጣ!
Federal Justice and Law Institute
https://t.me/lawsocieties