#እቁብን_ከሕግ_አንፃር
በሀገራችን እቁብ በእጅጉ የተለመደ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴ ነው።ይህ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴ በየመንደሩ፣ በየአካባቢው የዳበረ መሆኑን በምሳሌያዊ አነጋገራችን ጭምር ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው በሚል ዳብሮ እቁብ በመግባት እና በመቆጠብ የብርን መብረር መገደብ እንደሚቻል በማህበረሰባችን ዳብሮ እቁብ በቁጥር የተወሰኑ ሰዎች ስምምነት በማድረግና ለስምምነቱም ተገዢ በመሆን በቡድን ሆነው በተወሰነ ጊዜ የተወሰነ የገንዘብ መጠን በመሰብሰብ በየዙሩ የተሰበሰበውን ገንዘብ ስምምነት ያደረጉት ሰዎች በየተራ የሚወስዱበት ባህላዊ የቁጠባ ማህበር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
ከባንክ ወይም ከሌሎች የቁጠባ ማህበራት የሚለይበት በብዙ ነገሮች ሲሆን በተደራጀ ተቋማት የሚካሄድ ባለመሆኑ፣ ዘመናዊና የተደራጀ አሰራርን የማይከተል፣ ወለድ የማይከፈልበት፣የሚመራበት ሕግ ወይም ተቆጣጣሪ አካል ወይም በህግ የታወቀ መብትና ግዴታዎችን መቀበል የሚያስችል ሕጋዊ ሰውነት የሌለው ማህበር ነው።
በሕጋችን እቁብን በሚመለከት የተቀመጠ የተለየ የህግ ማእቀፍና ድንጋጌ የለም። እቁብ ከሁለት በላይ የተሰበሰቡ ሰዎችን የሚይዝ ማህበር ቢሆንም እንደ ማህበር ተመዝግቦ እውቅና ሊያገኝ እንደማይችል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 3(3) (ለ) መሰረት አዋጁ በዕድር፣ ዕቁብና መሰል ባሕላዊ ስብስቦች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል። በፍትሀ ብሔር ሕጉ የማህበራት ድንጋጌ መሰረትም መዝግቦ ለእቁብ እውቅና የሚሰጥ አካልም ስለሌለ እቁቦች ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ማህበራት ስላልሆኑ ሊከሱ ሊከሰሱ አይችሉም።
ነገር ግን እቁብተኞች የገቡት የውል ስምምነት አለ።የተወሰነውን ገንዘብ በየጊዜው በመክፈል በእጣ ወይም በስምምነነት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የተስማሙበትን ገንዘብ እንዲከፈላቸው ተስማምተዋል። ይህም በአባላቱ መካከል በተደረገው የውል ስምምነት መሰረት አባላቱ መዋጣት ያለባቸውን ግዴታ ማለትም የእቁብ ገንዘቡን የመክፈል እቁብ ወጥቶላቸው ገንዘብ የወሰዱ ከሆነም የወሰዱትን የእቁብ ገንዘብ ሙሉ እስኪመለስ ድረስ ገንዘቡን የመክፈል ግዴታ ያለባቸው ናቸው፡፡ይሄም ግዴታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1678 እና 1731 (1) መሰረት በህጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ህግ ናቸው በሚለው መሠረታዊ ከውል ህግ መሰረት ይመነጫል፡፡ በመሆኑም ግዴታዎች ይፈጠራሉ። የእቁብ ገንዘብ የበሉ ሰዎች የሚቀርባቸውን ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። ሰብሳቢው ከሌላው አባል በመሰረቱ የተለየ ግዴታ እና መብት የለውም መክንያቱም ሕጋዊ ሰውነት የሌለው ማህበር በመሆኑ ነው። ነገር ግን በዉላቸው ሰብሳቢው ከሌላው አባል የተለየ መብት እና ግዴታ እንዳለበት በውላቸው ካረጋገጡ ሰብሳቢውን ይሄንኑ ውል መሰረት በማድረግ መጠየቅ ይችላል።
ሌላው የእቁብተኞቹን ግዴታና መብቶች በፅሁፍ እንዲሆኑ የሚያስገድድ ሕግ ባይኖርም በፅሁፍ እንዲደረግ ይመከራል። የፅሁፉም ጥቅም በምን ያህል ጊዜ የእቁቡ ገንዘብ መከፈል እንዳለበት፣ ሳይከፈል ቢቀር ሀላፊነቱን ማን እንደሚወስድ፣ አባላት ከእቁቡ መውጣት ስለሚችሉበት ሁናቴ፣የከፈሉት ገንዘብ ተመላሽ መሆን አለመሆኑ ቀሪ ገንዘብ የመክፈል ግዴታን በተመለከተ አባላት ሊገደዱ የሚችሉት በግልፅ የሰጡትን ስምምነት መሰረት በማድረግ ወደፊት ለሚነሱ የህግ ክርክሮች እንደ ማስረጃ ያገለግላል።
በመጨረሻም የእቁብ ገንዘብ የበሉ ሰዎች ቀሪ ክፍያ ስለመክፈላቸው በፍታብሄር ህጋችን ከአንቀጽ 1920 ጀምሮ የተደነገጉትን አግባብነት ያላቸው የዋስትና ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የአንድነት አና የነጠላ ዋስትና በፅሁፍ፣ምስክሮች ባሉበት የገንዘቡ መጠን ተገልፆ ዋሶችን ማስፈረሙ በተለያየ ምክንያት እቁብ የበሉ ሰዎች ሲጠፉ ዋሱን ለመጠየቅ ስለሚረዳ በዚሁ አግባብ ማከናወን ይገባል።
ባጠቃላይ ወደፊት የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የእቁብተኞቹን መብትና ግዴታ የሚደነግግ ዝርዝር የውል ስምምነት ቢኖራቸው ይሄም ስምምነት ሁሉም እቁብተኞች በፊርማቸው እንዲያረጋግጡት ስንል እንመክራለን።
መልካም ቀን።
በማስረሻ የሺጥላ
ጠበቃ HenokTayeLawoffice
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/