TIKVAH-ETH:
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጉምሩክና የባንክ ስራ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። የባንክ ስራን ለማሻሸል የቀረበው አዋጅ 1159/ 2011 ሆኖ ሲጸድቅ የጉምሩክ አዋጅ 1160/2011 ሆኖ ጸድቋል።
የባንክ ማሻሻያ አዋጁ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በባንክ ዘርፍ ኢንቨስትመንት እንዳይሳተፉ ተጥሎ የነበረውን የህግ ክልከላ አንስቷል። ማሻሻያው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የውጭ አገር ዜጎች በባንክ ዘርፍ በመሳተፍ ለአገሪቷ ግንባታና ለውጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ነውም ተብሏል። አዋጁ በተጨማሪም ከወለድ ነጻ የባንክ ስራን ለማቋቋም እንደሚያግዝም ተጠቅሷል።
በተመሳሳይ የተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ በጊዚያዊ እቃ ማከማቻ መጋዘን እቃዎች የሚቆዩበትን ጊዜ ዝቅ በማድረግ የጉምሩክን አስተዳደር ቀላልና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ማሻሻያው ከዚህ በፊት የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቀረጥ ነጻ መብትን በተመለከተ ፈቃድ እንዲሰጡ የሚያስችለውን ደንብ በመሰረዝ የገንዘብ ሚኒስቴር ብቻ ፈቃዱን እንዲሰጥም ደንግጓል። ይህም የቀረጥ ነጻ እድሉ ለታለመት አላማ መዋሉን ለማረጋገጥና ለመከታተል እንደሚያስችል ተገልጿል።
Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia