#ትግራይ
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ ቢወስንም አልተተገበረም።
6 የVIP የጥበቃ አባላት የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚከካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " በመባል ተከሰዋል።
የመቐለ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሊቀመንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር ስርቆት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል።
ስድስቱ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ቤተሰቦቻቸው ብር ቢያስይዙም " ከላይ የመጣ ትእዛዝ " በሚል ከእስር አልተለቀቁም ብለዋል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች።
ባለፈው የግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ሳምንት መጨረሻ የሊቀ-መንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር " በጠባቂዎቻቸው ተዘርፏል " የሚል መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት ቢሰራጭም ደጋፊዎቻቸው " መረጃው የፈጠራ ወሬ ነው " በማለት ሲያጣጥሉ ቆይተዋል።
ሊቀ-መንበሩም በቅርቡ ከደጋፊዎቻቸው ጋር በነበራቸው ስብሰባ " አልተሰረቅኩም " የሚል እንደምታ ያለው በሚያሰመስል ሁኔታ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ታይተው ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia