አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ከአሜሪካን ጠበቆች ማህበር American Bar Association /ABA/ ጋር ውይይት ተደረገ
     የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ተ/ፕሬዚደንት እና የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት ም/ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው በአሜሪካን ሀገር ለግል ስራቸው በነበሩበት ከአሜሪካን የጠበቆች ማህበር American Bar Association (ABA) አመራሮች ጋር ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ::
  በእለቱም ከአሜሪካን የጠበቆች ማህበር የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ አካባቢያዊ ሀላፊ ከሆኑት #ብሌርታ ፒካሪ እና የኢንተርናሽናል ዴስክ ከሆኑት ጠበቃ ታይለር የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ABA ጋር በትብብር ሊያከናውኗቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል:: 
   በውይይታቸውም ሊደረጉ ስለሚችሉ የአቅም ግንባታ እና ተቋማዊ ድጋፎች ፤ የተከታታይ የህግ ስልጠና ትብብሮች ፤ በጥናትና ምርምር ዘርፍ፤ በህግ የበላይነት ዙሪያ ሊከናወኑ ስለሚችሉ ተግባራት ፤ በግልግል ዳኝነት መሰል ተያያዥ ርእሶች እንዲሁም በአጠቃላይ ተቋማዊ የልምድ ልውውጥ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል::
    እነዚህም በተለያየ መልኩ መግባባት ላይ የተደረሰባቸው ሆነው በቀጣይ ግንኙነቱ ቀጥሎ ወደ መግባቢያ ስምምነት MoU ማደግ እንደሚችሉና እንደሚገባ በአጠቃላይም ግንኙነቱ በዚህ መልኩ መጀመሩ በጣም  አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል::
      ABA ከተመሰረተ 140 አመት በላይ የሆነውና 400 ሺህ የሚጠጉ አባላትን የያዘ ከአሜሪካና አውሮፓ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፅእኖ ፈጣሪ የሙያ ማህበር መሆኑ ይታወቃል::
ቴዎድሮስ በአጭር ግዜ ጥያቄ ከአሜሪካን የጠበቆች ማህበር ጋር ለውይይት ያቀረቡት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በማግኘቱ እና ለዚህም ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::