#በአመክሮ_መፈታት_የሚቻለው_እንዴት_ነው?
=====================
አመክሮ የቅጣት ማስተማሪያነት ከሚገልጽባቸው ሁኔታዎች አንዱ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ተቀጪ ለፈፀመው ወንጀል የተፈረደበትን የእሥራት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ከመፈፀሙ በፊት የተወሰነ ጊዜ በመስጠት ቀሪውን የእስር ጊዜ ከእስር ውጩ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ የማድረግ ሥርዓት ነው አንድ ተቀጪ በአመክሮ ሊፈታ ይችል ዘንድ በወንጀል ሕጉ የተደነገጉት ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ይገባል፡፡

የቀጠለ 👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👉የወ/ሕ/ቁ 201 በተወሰነ ገደብ በአመክሮ መፈታትን አስመልክቶ መርህ አስቀምጧል፡፡ በአመክሮ መፈታት የተቀጪውን ፀባይ ማሻሻያ እና ወደደንበኛው ማህበራዊ ኑሮ መመለሻ ሆኖ መቆጠር እንደሚገባው ይገልፃል፡፡
በአመክሮ ለመፈታት ይቻለው ዘንድ አንድ ተቀጪ ከተፈረደበት ቅጣት 2/3ኛውን መፈፀም ይኖርበታል፡፡ የዕድሜ ልክ ጸኑ እሥራት ፍርደኛ ከሆነም ሃያ አመት ታስሮ ነው ጥያቄውን ማቅረብ የሚችለው፡፡ በአመክሮ የመፈታት ጥያቄ በተቀጪው ወይም “አግባብ ባለው አካል ለፍርድ ቤቱ ይቀርባል” (አንቀጽ202(1) “አግባብ ያለው አካል” ማነው የሚለውን ሕጉ አይመልስም እንደሚታወቀው በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ተብሎ እሥራት የተወሰነበት ሰው የሚቆየው ማረሚያ ቤት በመሆኑና የአመክሮ ጥያቄንም ለፍ/ቤት የሚያቀርበው ይኸው ተቋም በመሆኑ አግባብ ያለው አካል ማረሚያ ቤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሕጉ ግን ምናልባትም ወጣት ጥፋተኞች የሚቆዩበትንም ተቋማትና ሌሎችንም ታሳቢ ያደረገ ይመስላል፡፡
አመክሮን በሚመለከትም ማረሚያ ቤት ስለተቀጪው ፀባይ (አንቀጽ 202 (1) (ሀ)(ለ)) አጣርቶ ለፍ/ቤት ከሚልከው በተጨማሪ ተቀጪው ለደረሰው ጉዳት በተቻለ መጠን ሊከፍል የሚጠበቅበትን በፍርድ ቤት በተወሰነው መሠረት ወይም ከተበዳዮ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት ካሣ ለመክፈሉ ማረጋገጫ ማቅረብ እንደሚገባ በአንቀጽ 202(1)(ለ) ላይ ተመልክቷል፡፡ ነገር ግን በተግባር ይህ አይደረግም፡፡ ማረሚያ ቤቱ የተቀጪውን ፀባይ መሻሻል ፍርም ሞልቶ ከላከ ያለተጨማሪ ጥያቄ እስረኛው እንዲለቀቅ ይደረጋል፡፡
ሌላው በሕጉ ላይ የተመለከተውና በፍርድ ቤቶች ግን ሲተገበር የማይስተዋለው ጥፋተኛው ሲፈርድበት ቅጣቱን ከመፈፀሙ በፊት ቀደም ብሎ ሊለቀቅ እንደሚችልና ይህን እድል ለማግኘት ሊፈጽማቸው የሚገቡ ነገሮች እንደሚገለፁለት የተመለከተው ነው፡፡
እንደ ገደብ ውሣኔ ሁሉ በአመክሮ የሚለቀቅ ተቀጪም የፈተና ጊዜ ይሠጠዋል ይህም ማለት በተሠጠው የፈተና ጊዜ ውስጥ ፀባዩ ባይሻሻል ወይም ሌላ ወንጀል ሲፈጽም ቢገኝ (አንቀጽ 200 እና 206) በአመክሮ እንዲፈታ የተሰጠው ትእዛዝ ተነስቶ ተመልሦ እንዲታሠር ይደረጋል፡፡ በአመክሮ ቀርቶለት የነበረውን ቀሪ ቅጣትና ለአዲሱ ጥፋት የተወሰነበትን ጊዜ ይታሠራል፡፡
የፈተናው ጊዜ እንደወንጀሉ ክብደት እየታየ የሚሠጥ ነው፡፡ በመርህ ደረጃ የፈተና ጊዜ የሚለው ሳይፈፀም የቀረው የእሥራት ጊዜ ማለትም 1/3ኛው የቅጣት ዘመን ነው፡፡ በአመክሮ ተቀጪው እንዲለቀቅ ፍ/ቤት ሲያዝ የፈተናው ጊዜ ቢያንስ ሁለት ዓመት ሲሆን ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ነው፡፡ በአመክሮ የመፈታት ዕድል ያገኘው ተቀጪ የዕድሜ ልክ እስረኛ ከሆነ ግን የፈተና ጊዜው ከ5 ዓመት ማነስ ና ከ7 ዓመት መብለጥ የለበትም (አንቀጽ 204)፡፡
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/