አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጥቆማ አድርሱ
~~8482🛑

ህብረተሰቡ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ሲመለከት #በ8482 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1112/2011 የአልኮል ምርት በማንኛውም በብሮድካስትና ቢል ቦርድ ማስተዋወቅ የተከለከሉ ድንጋጌዎች መውጣቱን ተከትሎ አብዛኛው የአልኮል ምርት አምራቾች ህጉን ተከትሎ በአ/አ ስታዲየም ዙሪያና በተለያዩ ቦታዎች የተሰቀሉ ቢልቦርዶችን #በማንሳት ላይ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። ሆኖም በአንዳንድ ቦታዎች እስካሁን ድረስ የቢልቦርድ ማስታወቂያ ያልተነሱ መሆኑንና የአልኮል አምራች ድርጅትና የማስታወቂያ ሰሪ ድርጅቶች በየቦታው የተሰቀለውን ቢልቦርድ እንዲያነሱ አሳስቦ ህብረተሰቡም በየቦታው የተሰቀሉ ቢልቦርዶች ሲመለከት በ8482 በመደወል #ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።

√√በህዝብ ተወካዬች ም/ቤት በቅርቡ በፀደቀውን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ 1112 መሰረት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ የአልኮል ማስታወቂያዎችን በብሮድካስት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ህግ ተግባራዊ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል ።

#8482

የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ስትመለከቱ #በ8482 በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡ ተጠይቃችኃል።
Via waltainfo.com