አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሚስትን የልደት ቀን መርሳት ያስቀጣል…
🔥🆕🚨
የዓለም ሀገራት የሚመሩበት እና የሚተዳደሩበት ሕግ አላቸው። አንዳንድ ሕጎች ግን አስገራሚ ናቸው። የሚከተሉት ሀገራት ሕጎች ደግሞ ከተለመደው ወጣ ካሉት መካከል ይጠቀሳሉ።


🚫 የሚስትን የልደት ቀን መርሳት

#ሳሞኣ በምትባል ደሴት ሀገር የሚስትን የልደት ቀን መርሳት ወንጀል ነው። በሀገሪቱ ሕግ ባል የሚስቱን ልደት ከረሳና ሚስትም ለፖሊስ ቅሬታ ካቀረበች ባል ከቅጣት አይድንም። ባል ለመጀመርያ ጊዜ ከሆነ የረሳው ከፖሊስ የቃል ማስጠንቀቂያ ይደርሰዋል። ነገር ግን በድጋሚ ከረሳ በእስራት የሚያስቀጣው ወንጀል ይሆናል።

🚫 ለልጅ በሕግ ያልተፈቀደ ስም ማውጣት

#አይስላንድ ሀገር ልጅ ስድስት ወር ሳይሞላው ስም ሊሰጠው ይገባል። የሚሰጠው ስም በሕግ የተመዘገበ አይስላንዳዊ ስም መሆን ይጠበቅበታል። ይህም በሕግ ይረጋገጣል። ስም መስጠትን በተመለከተ በሀገሪቱ ልዩ የሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል።

ለህጻኑ በብሔራዊ የሰዎች መዝገብ ላይ ያልተዘረዘረ ስም እንዲሰጠው ከተፈለገ፣ ስሙን ለማጽደቅ ለግል ስሞች ኮሚቴ ማመልከቻ ማቅረብ ይጠበቃል። ከዚያ በፊት ያልተመዘገበ አዲስ ስም እንደመሆኑ መጠን ለማስመዝገብም ተገቢውን ክፍያ መፈጸም ግዴታ ነው።

🚫 የቆሸሸ መኪና መንዳት

#ሩሲያ ውስጥ የቆሸሸ መኪና እየነዱ ከተያዙ ፖሊስ እርስዎን ለመቅጣት አያቅማም። ስለዚህ እስከ 2 ሺህ የሩሲያ ሩብል ቅጣት ለመክፈል ዝግጁ መሆን ይጠበቅቦታል። ከማሽከርከርዎ በፊት ማሳጠብ ግድ ነው። ይህ ሕግ በሩሲያ ብቻ ሳይሆን በፊሊፒንስ እና ቤላሩስ ተግባራዊ ይደረጋል።

🚫 ፓርላማ ውስጥ መሞት

#እንግሊዝ ፓርላማ ውስጥ መሞት የተከለከለ ነው፡፡ የፓርላማ አባላትን ጨምሮ በንጉሣዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ የሞተ ሰው ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የማግኘት መብት አለው የሚል አፈ ታሪክ በመኖሩ በዚያ መሞት ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ስለዚህ ወደ እንግሊዝ ፓርላማ የሚገቡበት አጋጣሚ ካለ ስለ ሙሉ ጤንነትዎ እርግጠኛ ይሁኑ። ጥሩ ስሜት ካልተሰማዎት በጭራሽ ወደዛ አይጠጉ።

🚫 ማስቲካ መሸጥ እና ማኘክ

#በሲንጋፖር ለሕክምና ዓላማ ካልሆነ በስተቀር ማስቲካ መሸጥም ሆነ ማኘክ ሕገወጥ ነው። የሲጋራ ቁራጮች፣ የከረሜላ መጠቅለያዎችንም ሆነ ሌሎች መሰል ቆሻሻዎችን መጣልም የሚያሥቀጡ ተግባራት ናቸው። በትንሹ ከ500 ዶላር ያላነሰ ክፍያ ያስቀጣሉ። እንደ ድርጊቱ ተደጋጋሚነትም ቅጣቱ ይጨምራል።

🚫 በምሽት ማፏጨት

#በቱርክ በምሽት ማፏጨት የተከለከለ ነው። ይህም በድሮ ጊዜ በምሽት ማፏጨት ክፉ መንፈስ ይጠራል ተብሎ ስለሚታሰብ የወጣ ሕግ ቢሆንም አሁን ላይ በምሽት የድምጽ ብክለት እንዳይኖር ይረዳል በሚል እስካሁን ጥቅም ላይ ይውላል።
#FANA
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26😁113👏1