አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አዲሱ የተሿሚወች የደመወዝ ጥናት.pdf
14.9 MB
አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ትግበራ መስከረም 1 ሊጀምር ነው

- ለደሞዝ ጭማሪው ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ ተመድቧል

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን መምጣት ተከትሎ በመንግስት ቃል ከተገቡት ጉዳዮች አንዱ የሆነው የደሞዝ ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን በኢትዮጵያ ቼክ የተረጋገጠ አንድ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጠቁሟል።

ባለፉት ሰአታት ውስጥ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይህ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ነው የተባለ ምስል እንዲሁም አዲሱን የደሞዝ ስኬል ያሳያል ተብሎ የተገለፀ ስሌት በስፋት ሲያጋሩ ቆይተዋል።

ደብዳቤው በሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተፈረመ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ለጠ/ሚር ቢሮ ተልኮ ሲቪል ሰርቪስ ደግሞ ኮፒ እንደተደረገ ይገልፃል።

ኢትዮጵያ ቼክ የደብዳቤውን እና የደሞዝ ስኬሉን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን ለታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ እንደተመደበ እና ጭማሬው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ይገልፃል።

ይህ በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ተመላክቷል።

በአዲሱ ስሌት መሠረት ነባር ደሞዛቸው በጣም ዝቅተኛ የነበረው እና 1,100 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ332 ፐርሰንት ጨምሮ 3,660 ብር እንደሚሆን ያሳያል።

በሌላ በኩል ደሞዛቸው ከፍተኛ የነበረው እና 20,468 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ5 ፐርሰንት ጨምሮ 2,1491 ብር እንደሚሆን ይጠቁማል።
#ምንጭ:- ኢትዮጵያ ቼክ
https://t.me/AleHig