" የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ በደንብ ማረጋገጥ አለባቸው " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን አሳወቀ።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉንም ገልጿል።
ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው " ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት " አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።
የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው 3 ግለሰቦች #ሙሉ_ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተም እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ ያረጋግጣል።
ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራም ተጠርጣሪዎቹ ፦
- ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣
- ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን ፣
- በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣
- በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶች
- የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።
ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ አስታውሷል።
" መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው " ያለው ፖሊስ መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ለወንጀሉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት የተከራዮቻችውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig
https://t.me/lawsocieties
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig