Forwarded from ሕግ ቤት
ጀማሪ ጠበቃ የመቅጠር 7 ጥቅሞች‼️
1. የፍርድቤቱ ቀጠሮ 4:00 ሆኖ 2:30 ደርሶ በር ያስከፍታል።😂
2. ስልክ ሲደወልለት ገና ጭርር ከማለቱ በግማሽ ጥሪ ያነሳል።😂
3. በጣም ለቀላል ጉዳይ ከሀገር ውስጥ ሕግ እስከ አለምአቀፍና አህጉራዊ ተጓዳኝ ሕጎች ያነባል።😂
4. ጉዳዩ መልስ ለመቀበል ወይም ብይን ለመስማት (ምንም ክርክር የሌለው ቀጠሮ) ቢሆንም እንኳን እንደ ማትሪክ ተፈታኝ ለሊቱ አጋማሽ ድረስ ይቸክላል።😂
5. ጀማሪ ጠበቃ የሀገሪቱን የወደቀ የፍትህ ሲስተም በጫንቃው ተሸክሞ ይጎብጣል፣ያዝናል፣ የሆነ ነገር አድርጎ ለማስተካከልና ለውጥ ለማምጣት ያልማል።😂
6.ይዘንጣል፣ሽክ እምሽክ ይላል፣ጸጉሩን ጢሙን ይቆረጣል፣ሴቷም ሁሌም ፀጉሯን ትተኮሳለች።😂
7. ደንበኞቹን በሸራተን ደረጃ ይንከባከባል 😂
8. ቆይ ግን ነባር ጠበቆች ለምንድነው ቀስ ብላችሁ የማትራመዱት? እግዞ ፍጥነት! እግረመንገዳችሁን የጠበቃ ፈጣን አረማመድ ስልጠና የሚሰጥ ተቋም ካለ ጠቁሙንማ ኤሊነት እየተሰማን ነው።😂
ሰናይ ሰኞ ጓደኞቼ!
በጠበቃ Mesi Bahiru
#ሕግቤት
የሕግ ቤተሰብ
https://t.me/Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍45😁28👏2🤣1