..............#ለግልጸኝነት እንዲረዳና ካልተገባ አሰራር ነጻ ለማድረግ አዋጁ ዝርዝር የሆነ የጨራታ አካሄድንም አካቶታል።
ጨረታ የከተማ መሬት ማስተላለፊያ ሆኖ በመርህ ቢቀመጥም እንደልዩ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ላላቸው አካላት መሬት በምደባ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ምደባ የሚለውን ሀሳብ አዋጁ ሲተረጉመው በጨረታ ሊስተናገዱ ለማይችሉ ተቋማት በመሬት ላይ የመጠቀም መብት በሊዝ የሚተላለፍበት ስልት ነው ይለዋል፡፡ መሬት በምደባ ሲተላለፍ የሊዝ መነሻ ዋጋ ይከፈል አይከፈል አዋጁ ላይ አልተገለጸም፡፡ ሆኖም ግን ስለሊዝ መነሻ ዋጋ በግልጽ የተቀመጠው በአንቀጽ 12(3) ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ የሆኑ የቀበሌ ቤት ነዋሪ የነበሩ ተነሽ በሚሆኑበት ጊዜ ምትክ ቤት መስጠት ካልተቻለ ቤት የሚሰሩበት ቦታ በምደባ ተሰጥቷቸው የሊዝ መነሻ ዋጋ መክፈል እንዳለባቸው ነው፡፡
በምደባ የከተማ ቦታ የሚሰጣቸው አካላት አንቀጽ 12 ስር ተዘርዝረዋል፡፡ እነሱም፡- ለባለበጀት የመንግስት መስሪያ ቤት ለቢሮ አገልግሎት፣ በመንግስት ወይም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሚካሄዱ ማህበራዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ በመንግስት ለሚካሄዱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ለራስ አገዝ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታወች፣ ለእምነት ተቋማት አምልኮ መፈጸሚያ፣ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪወች ልማት፣ ለኤምባሲወችና ለአለምአቀፍ ድርጅቶች አገልግሎት፣ በተለዩ ልዩ አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውሉ ቦታወች ናቸው፡፡
የሊዝ መብትን ስለማስተላለፍ
ልክ እንደሌሎች የንብረት መብቶች የሊዝ መብትንም ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን በኢትዮጵያ ህግ ግን የተወሰኑ ገደቦች ተቀምጠውበታል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 24(1) ላይ የከተማ ቦታ ላይ የሊዝ ባለይዞታ የሆነ ሰው የይዞታ መብቱን ማስተላለፍ ወይም በከፈለው የሊዝ ክፍያ መጠን ልክ በዋስትና ለማስያዝ ወይም በካፒታል አስተዋጽኦነት መጠቀም እንደሚችል ተደንግጎ ይገኛል፡፡ እዚህ ላይ መረዳት የሚገባው በተከፈለው የሊዝ ክፍያ መጠን ልክ የሚለው የሚያገለግለው መብቱን በዋስትና ማስያዝ ወይም በካፒታልነት ለመጠቀም እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ግንባታው ሳይጠናቀቅ ለሚሸጥ ግንባታ ነው፡፡
#የሊዝ ውል ምስረታና ይዘት
በአዋጁ መሰረት የከተማ መሬት በሊዝ እንዲይዝ የተፈቀደለት ማንኛውም ሰው አንቀጽ 16 እንደተመለከተው ከሚመለከተው አካል ጋር የሊዝ ውል ማድረግ አለበት፡፡ የሊዝ ውሉም ግንባታው የሚፈጸምበትን ጊዜ፣ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ፣ የክፍያ አፈጻጸም ሁኔታ፣ የችሮታ ጊዜ፣ የውል ሰጭና ተቀባይ መብትና ግዴታ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝር ሁኔታወችን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ እንደውል ሁሉ በአዋጁ የተቀመጠ ልዩ ድንጋጌ ከሌለ በስተቀር በፍትሐ ብሔር ህጉ ላይ ያለው ጠቅላላ የውል ድንጋጌወች ለሊዝ ውልም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የሊዝ ውል አካል ከሆኑት መካከል አንዱና ዋናው የሊዝ ዘመን ነው፡፡ የሊዝ ዘመን እንደከተማው የእድገት ደረጃና የልማት ስራው ዘርፍ ወይም የአገልግሎቱ አይነት የሚለያይ ሆኖ ከ15 እስከ 99 አመት ሊደርስ እንደሚችል በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
#የሊዝ ውል መቋረጥ
#በአዋጁ አንቀጽ 25 ላይ የሊዝ ውል የሚቋረጥባቸው ሶስት ሁኔታወች ተቀምጥል እነርሱም፡-
ባለይዞታዉ በሊዝ የተለከበዉን ቦታ በሊዝ ዉሉ ላይ በተገለጸው አግባብ አለመጠቀም(ውልን አለማክበር) ፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል እና የሊዝ ዘመን ሲያበቃና ሳይታደስ ሲቀር ናቸዉ፡፡
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/