ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል/ጫፍ ሁነው ተገልጋዮች ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጪዎች ሳይዳረጉ ጥራት ያለው አገልግሎት እና ፍርድ ማግኘት እንዲችሉ ፍ/ቤቱ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያለማቸውን
ዘመናዊ የፍርድ ቤት ስርዓት አስመረቀ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የፍርድ ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል፣
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያለማቸውን አውቶማቲክ ትራንስክሪፕሽን፣ ስማርት ቻትቦት እና ዲጂታል የመረጃ ዴስክ የያዘ የስማርት ኮርት ሩም ሲስተም በታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ ባስተላለፉት መልዕክት የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎቹ ለፍ/ቤቱ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአገራችን ህዝብ ደስ የሚያሰኝ እና ተስፋ የሚሰጥ ምዕራፍ መሆኑን በመግለፅ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተጠናክረው በሁሉም ደረጃ ባሉ ፍ/ቤቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ክቡር አፈ ጉባኤው አክለውም የመንግስትና የህዝብ ሃብት ሳይባክን፣ ተገልጋዮችም ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጪዎች ሳይዳረጉ ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ እንዲሁም በአገልግሎቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በግልጽና በቀላሉ በማቅረብ ፈጣን ምላሽ ማግኘት እንዲችሉ የሚያግዙ የጤክኖሎጂ መተግበሪያዎቹ ከመሆናቸውም ባሻገር የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከመሰረቱ የሚፈቱና መንግስት በትኩረት የያዘውን አገራዊ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እቅድ ስኬታማ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ባደረጉት ንግግር የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና የዳኝነት ስርዓቱን ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን ለማድረግ የተደራጀ እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ከመዘርጋት አኳያ በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁ ገልጸው ላለፈው አንድ አመት ያህል ገደማ ሲሰራባቸው ቆይተው የተመረቁት የአውቶማቲክ ትራንስክሪፕሽን (ንግግርን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ስርዓት)፣ ስማርት ኮርት ሩም (በቴክኖሎጂ የተደገፈ ችሎት)፣ ስማርት ቻት ቦት (የውይይት መለዋወጫ ሮቦት) እንዲሁም መረጃ መስጫ (ኢንፎርሜሽን ዴስክ)ቴክኖሎጂዎች ወደ ስራ ሲገቡ በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በእጅጉ እንደሚቀንሱ ገልፀዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ በቀጣይ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የተጀመሩ የዳኝነት ስርዓቱን በዲጂታል የታገዘ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች በሂደቱ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የዳኝነት አገልግሎትን የተቀላጠፈና ለዜጎች ተጠቃሚነት ምቹ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ ለምረቃ የበቁት የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በዳኝነት ስርዓቱ በስፋት እንዲተገበሩ በቀጣይም ከፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የኢትዬ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚን በመወከል ንግግር ያደረጉት ቺፍ የቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ታሪኩ ደምሴ በበኩላቸው እነዚህ እና ሌሎች የዳኝነት ስርአቱን ለማዘመን የለሙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር የሚያስችል አስተማማኝ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የፍትህ ስርአቱን በእጅጉ ለማሻሻል የሚረዳ ይሆናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር የፍርድ ቤቱን አሰራር የሚያልቁ ደህንነታቸዉ የተጠበቀ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት እና የዳኝነት አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ አዉቶሜት (Automate) በማድረግ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት የሚያቀላጥፉ የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ ስርዓት እና ኤሌክትሮኒክ መዛግብት አስተዳደር ስርዓት እንደሚተገበሩ ጠቁመዋል።
በዝግጅቱ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎቹ አተገባበር የተመለከተ ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ለታዳሚ እንግዶች ሰፊ ገለጻ በባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
#Federalsupremecourt
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
‹‹የስማርት ኮርት ሲስተም››

👍4❤3👏1
I am delighted to meet Her Excellency Mrs. #MeazaAshenafi, former President and Chief Justice of the Federal Supreme Court of Ethiopia, at the African Union. #MeazaAshenafi
#President, #FederalSupremeCourt #Ethiopia #SupportWomeninLaw
#SayYesToEqualPay #SayYesToEqualPromotion
#WomenInCharge
#ChampionWomenLeaders.
#womeninleadershipmatters
#herleadershipcounts
#HeforShe #EqualPay #EqualityCantWait #Inspireinclusion
#GenderEquality #WomenInLaw #IAWL9 #LegalEmpowerment #AU #GenderJustice #WomenLeadership #EqualityInLaw #ChampionWomenLeaders #HerLeadershipCounts
IAWL ~ Institute for African Women in Law

❤20👍8👎6🔥2👏2