አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ እንዲጸድቅ የሚጠይቅ ሪፖርት
ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብት ምክርቤት ቀረበ!

ይህ ሪፖርት በኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ አይነስውራን ማህበር በጋራ ተዘጋጅቶ ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብቶች ምክርቤት የቀረበ ሲሆን፤ የማህበራቱ የጋራ ሪፖርት በየግዜው እየጨመረ  የመጣውን በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰት በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ በመተንተን፣ በአጥፊዎች ላይ  አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ  ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይጠይቃል።  የጋራ ሪፖርቱ  የኢትዮጵያ መንግስት፣ በእኩልነት መብት እና ከአድልዎ በመጠበቅ መብት፤ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች መብቶች፤ በሥራ እና በቅጥር መብት፤ እንዲሁም  ተደራሽነትን በተመለከተ የህግ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት  የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች ስምምነት ተጨማሪ ፕሮቶኮልን እንዲቀበል፤ የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞችን ፕሮቶኮል እንዲቀበል እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅን የአካል ጉዳተኞችን ማህበራት ጉልህ ተሳትፎ ባረጋገጠ ሁኔታ እንዲወጣ ምክረሀሳብ ያቀርባል።
በጋራ ሪፖርቱ ውስጥ የተመላከቱ ቁልፍ ምክረሀሳቦች በአራተኛው ሑሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (UPR) መድረክ በተ.መ.ድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንደምክረሀሳብ ሖነው በምክር ቤቱ ሀገራት እንዲነሱ ለማስቻል ኢንባሲያቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ሀገራት ሪፖርቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ እና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግንዛቤ እንዲያገኙ ጠንካራ  ተግባራጥ በትኩረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
ከ Ethiopian center for disability and development (ECDD)
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9
................👇👇👇👇👇
👉በወንጀልም ሆነ በፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ላይ ለምስክርነት ስንጠራም እነኚህን ጉዳዮች ልብ ማለት እና ሕግ የጣለብንን ግዴታ መወጣት ይጠበቅብናል።

1.መጥሪያን መቀበል

የሚላክልን መጥሪያ ለምን ጉዳይ፣ መቼ እና የት እንደተጠራን ይገልፅልናል። ስለ ጉዳዩ እንኳን ባናውቅ የተላከልንን መጥሪያ አልቀበልም ማለት አይገባም፡፡

ፍርድ ቤቱ መጥሪያ አልቀበልም ማለታችንን ካረጋገጠ ታስረን በግድ እንድንቀርብ ትዕዛዝ ሊያስትላልፍብን ይችላል። ስለዚህ ግልፅ ያልሆነልን ወይም መጥሪያው አይመለከተኝም የምንል ከሆነ መጥሪያውን ተቀብለን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት ቀርበን ማስረዳት ወይም ማጣራቱ ተገቢ ነው።

2.ቀጠሮ ማክበር

ማንኛውም መጥሪያ ከደረሰን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት በፍርድ ቤቱ መገኘት አለብን። በፍርድ ቤቱ ስንጠራም በአካል መቅረብ እና መቅረባችንን ማሳወቅ አለብን። ፍርድ ቤቱ ሳያሰናብተንም ችሎቱን ለቅቀን መሄድ አንችልም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- 👇👇👇👇👇👇👇
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7390

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121